ዜናፖለቲካ

ዜና: ብልጽግና እና አብንን ጨምሮ 11 ፖለቲካ ፓርቲዎች የተጋነነ የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባላት እንዳላቸው ቢገልጹም ማስረጃ አላቀረቡልኝም - ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 21 ፖለቲካ ፓርቲዎች የተጋነነ ቁጥር ያለው የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባሎላት ቁጥር እንዳላቸው ቢያሳውቁም ማስረጃ ሲጠየቁ ማቅረብ አልቻሉም ሲል ባወጣው መግለጫ ተቸ።

ቦርዱ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ለሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግሥት የሚመደብ በጀትን ባለፉት ሶስት አመታት ማከፋፈሉን አስታውቆ አንደኛው መስፈርት ፓርዎቹ ያላቸው የሴቶች እና የአካል ጉዳተኛ አባልት ቁጥር መሆኑን ጠቁሟል።

“የበጀት ድጋፍ ለማከፋፈል በሕጉ ከተቀመጡ መሥፈርቶች መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሏቸውን ሴት እና አካል ጉዳተኛ አባላት ቁጥር በቃለ-መኃላ አስደግፈው ማቅረብ” የሚለው እንደሚገኝበት የጠቆመው ቦርዱ በዚህም መሠረት “21 ፖለቲካ ፓርቲዎች በ2016 ዓ.ም. ለቦርዱ ያሳወቁት የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባሎቻቸው በ2014 እና 2015 ዓ.ም ካቀረቡት ቁጥር አንጻር የተጋነነ ሆኖ ማግኘቱንም” አስታውቋል።

ፓርቲዎቹ የእነዚህኑ አባሎቻቸውን ሙሉ መረጃ ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ቦርዱ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ማሳወቁን ጠቁሞ ከዚህ ውስጥ 10 ፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ምላሾችን የሰጡ እና በእጃቸው የሚገኙ መረጃዎችን ማቅረባቸውን ገልጿል።

11 ፓርቲዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ከ10,000 እስከ 900,000 የሴት አባላትና የአካል ጉዳተኛ አባላት ቁጥር ማቅረባቸውን የጠቆመው ቦርዱ ተገቢውን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠየቁም ምላሽ አልሰጡኝም ብሏል።

የ11 ፖለቲካ ፓርቲዎቹን የስም ቦርዱ ባወጣው መግለጫ በዝርዝር አስቀምጧል፤ እነዚህ ፓርቲዎች ይህ መግለጫ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሴት እና የአካል ጉዳተኛ የአባሎቻቸውን መረጃ እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ይህ የማይፈጸም ከሆነ ቦርዱ ተገቢውን ሕጋዊ ዕርምጃ እወስዳለሁ ሲልም አስጠንቅቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ ብልጽግና ፓርቲ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄሸ፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ ራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት፣ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ናቸው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button