ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 22/ 2016 ዓ/ም፦ ትውልደ ኢትዮጵያዊ_አሜሪካዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በሰብል ልማት ላይ ጉልህ አስተዋጸኦ ላደረጉ ተመራማሪዎች እውቅና የሚያበረክተው የፐርዱ ዩኒቨርሲቲ “ሌጀንድስ ኦፍ አግሮኖሚ ሽልማት” የአመቱ ተመራማሪ ሆነው ተመረጡ

በግብርና ምርምር ሥራ የዩኒቨርሲቲው የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ በመሆን እውቅና የተሰጣቸው ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር)  በተለያየ ጊዜ በአካሄዱት ምርምር “ሃይብሪድ” የሆኑ የማሽላ ዘሮችን መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ተመራማሪ ናቸው።

በተለያየ ጊዜ 17 ከፍተኛ ሽልማቶችን የተጎናጸፉት ፕሮፌሰሩ ጥቅምት ወር  ከ 21 አሜሪካውያን መካከል አንዱ በመሆን የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን  ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ነው። 

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ በምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዚህ በፊት ከዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑም የሚታወቅ ነው።

በተጨማሪም “ኦርደር ኦፍ ግሪፊን እና ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” የተሸለሙት ፕሮፌሰሩ ከምርምር ሥራቸው በተጨማሪ ከ70 በላይ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማማከር ከ200 በላይ የምርምር ውጤቶችን ለኅትመት አብቅተዋል፡፡

የሮክፌለር ፋውንዴሽን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዲሁም የአሊያንስ ግሪን ሪቮሉሽን የክብር አባል ለመሆንም በቅተዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከሮክፌለር፣ ከሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በትብብር የሚሠሩት ተመራማሪው፤ የሣይንስ ካውንስል፣ የሣሣካዎ ግሎባል የቦርድ አባልም ናቸው፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button