ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኦብነግ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አድርገዋል የተባለውን ንግግር "የሰላም ስምምነቱን የሚጥስ” ሲል ተቃወመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3/ 2017 ዓ/ም፦ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ)፤ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፓርቲውን በተመለከተ አድርገዋል የተባለውን ንግግር “የሰላም ስምምነትን የሚጥስ” ሲል ተቃወመ።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ባወጣው መግለጫ፤ በጷጉሜ 3/2016 ዓ.ም. በኢትዮ ፎረም ሚዲያ በተሠራጨው ቪዲዮ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ፓርቲውን “በግብጽ የተፈጠረ የኢትዮጵያ ጠላት” ሲሉ ተደምጠዋል ብሏል።

የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አድርገዋል የተባለውን ንግግር “ቀስቃሽ” ሲል የተቃወመው ኦብነግ፣ “መሠረተ ቢስ” እና “በሕጋዊነቱ ላይ የተቃጣ” ሲልም ፈርጇል።

ፓርቲው የፊልድ ማርሻሉን ንግግር እ.ኤ.አ በ2018 በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በአስመራ ኤርትራ የተፈረመውን “የሰላም ስምምነት መንፈስ የሚጻረር ነው” በማለት እንዳሳሰበው ገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት “የዚህን ቪዲዮ ትክክለኛነት በአስቸኳይ እንዲያጣራ እና ንግግሩ በስህተት የተተሮገመ ከሆነ በይፋ ውድቅ እንዲያደርግ” ጠይቋል። 

ነገር ግን ትክክለኛ ኾኖ ከተገኘ መንግስት “ከዚህ ጎጂ አስተያየት ራሱን በማራቅ ለሰላም ሂደቱ ያለውን ቁርጠኝነት ባስቸኳይ እንዲያረጋግጥ” አክሎ ጥሪ አቅቧል።

ኦብነግ በመግለጫው ለሰላም ሂደቱ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጾ፤ የሶማሌ ህዝብ በአለም አቀፍ ህጎች እና በኢትዮጵያ ህገ መንግስት እውቅና ያገኘውን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብቱን ሰላማዊ በሆነ የፖለቲካ መንገድ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት ዝምታም ሆነ እርምጃ አለመውሰድ ተቀባይነት እንደሌለው ጠቁሞ ይህም ፓርቲው ወደ ፊት ሌሎች አማራጮችን እና እርምጃወችን ለማየት ሊዳርገው እንደሚችል ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button