ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ኦፌኮ በአቶ በቀለ ገርባ ምትክ አቶ ሙላቱ ገመቹን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም፡- የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) በአቶ በቀለ ገርባ ምትክ አቶ ሙላቱ ገመቹን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡን አስታወቀ፤ በክልሉ በሚገኙ 22 ዞኖች አሁንም ውጊያ እየተካሄደ ነው ብሏል።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን ባሳለፍነው ሳምንት ማገባደጃ ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂዷል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ከስብሰባው መገባደድ በኋላ ባወጣው መግለጫ አጠቃላይ ሀገራዎ በሆኑ እና በኦሮምያ ወቅታዊ ሁኔታዎች መምከሩን አመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ከመቸውም ግዜ በላይ አዳጋች ሁኗል ሲል ገልጿል። የሀገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ እየተበላሸ ነው ሲል የገለጸው ኦፌኮ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ደግሞ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ነው ሲል ኮንኗል።

ካለፉት የሀገሪቱ ስርአቶች በመማር የዲሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመምራት ይልቅው ገዢው ፓርቲ የተወሰኑ ቡድኖችን ጥቅም ማስጠበቂያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ሲል የተቸው ኦፌኮ ብልጽግና የሀገሪቱን ህገመንግስት ወደ ጎን አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው፣ ሰብአዊ መብቶች እየገፈፈ እና ጦርነት በሁሉም ቦታ እንዲስፋፋ እያደረገ ነው ሲል ገልጿል።

አሰቃቂ ግድያዎች፣ የመንደሮች ሙሉ በሙሉ መቃጠል፣ የዋጋ ንረት፣ ስልታዊ ሙስና፣ ተላላፊ በሽታዎች ማገርሸትና መስፋፋት፣ ረሃብ፣ እና ስራ አጥነት በሀገሪቱ እየተንሰራፋ ይገኛል ሲል አስታውቋል።

በኦሮምያ በሚገኙ 22 ዞኖች በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች መካከል አሁንም ውጊያ እየተካሄደ ነው ሲል ከዞኖቹ ያገኘውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኦሮሚያ ክልል እስር፣ ድብደባ፣ መፈናቀል፣ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በጅምላ ማቃጠል፣ የአርሶ አደሩን ከብቶች ግድያ፣ ሰዎችን በህይወት እያሉ ማቃጠል እና ሌሎችም አሰቃቂ ግድያዎች በመንግስት ታጣቂዎች የሚፈጸሙ የዕለት ተዕለት ተግባር ሆነዋል ብሏል።

በሁሉም የኦሮምያ ዞኖች መንግስት ድሮን በመጠቀም የንጹሃንን ህይወት እየቀሰፈ ነው ሲል አስታውቋል፤ በተለይም ደግሞ በሸዋ እና በአርሲ ዞኖች እንዲሁም በቡኖ በደሌ ሁኔታው የካፋ ነው ሲል ገልጿል። አስተማሪዎች እና ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ እያሉ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በድሮን ተገድለዋል ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button