ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ

ዕለታዊ ዜና፡ ከ220 በላይ የቀድሞ የደቡብ ክልል የመንግስት ሠራተኞች የተመደቡበት የስራ ዘርፍ ባለመኖሩ ቅሬታ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29/ 2015 ዓ.ም፡- በሲዳማ ክልል መንግስት ውስጥ ከተመደቡ 349 የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ 223 የሚሆኑ የቀድሞ የደቡብ ክልል ሠራተኞችን ክልሉ አልቀበልም በማለቱ ሠራተኞቹ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ይህ ውሳኔ የተላለፈው የሲዳማን ቋንቋ አትችሉም በሚል ከዚህ ቀደም ባልነበረ የሰራተኞች ምደባ አሰራር በደል ተፈፅሞብናል ማለታቸውን የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዘግቧል፡፡ ቅሬታቸውንም ለማቅረብ ወደ ቀድሞው ደቡብ ክልል አስተዳደር ጽ/ቤት ማምራታቸውን በዘገባው ተካቷል፡፡                                                                                                             

ሠራተኞቹ እንደ ፍላጎታቸው በሲዳማ ክልል ቢመደቡም የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ የክልሉን ሕገ-መንግስት በመጣስ ያሳለፈው ውሳኔ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

ከክልሉ የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የቀድሞውን ጨምሮ የሲዳማ ክልል 1,327 ሰራተኞች፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 1,029፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 1,958 እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደግሞ 2,320 ሠራተኞችን እንዲቀበሉ ተወስኗል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button