ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎችም ሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2016 .ም፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ እና ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎችም ሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

ሐሰተኛ ሰነድ ያላቸው እና ምንም ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን በተደረገ ማጣራት አረጋግጠናል ሲሉ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውነ ኢቲቪ ዘግቧል።

እነዚህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያነሡት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውነ አስታውቋል።

በተለያየ ምክንያት ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ዜጎች ለማጣራት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል ያለው ዘገባው በኢትዮጵያ ዜጎች እየተጠቀሙበት የሚገኘውን ፓስፖርት ኤሌክትሮኒክ (ኢ-ፓስፖርት) ለማድረግ እና ለማዘመን እየተሠራ ስለመሆኑም ጠቁሟል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button