ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በእምነት ተቋማት የሚስተዋሉ ፖለቲካዊ ይዘት የጎላባቸው ስብከቶችና ትንታኔዎች በአፋጣኝ ሊታረሙ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ለሃይማኖታዊ ተግባርና ዓላማ በሚደረጉ ስብስቦች እና በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያ በኩል ተገቢ ያልሆኑ ስብከቶች እየተስተዋሉ እንደሚገኙ አስታወቀ።  

የሃይማኖት ተቋማት መሠረታዊ ተልዕኮና ዓላማ በማይስማማ አኳኋን ለሃይማኖታዊ ተግባርና ዓላማ በሚደረጉ ስብስቦች እና በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያ በኩል ተገቢ ያልሆኑና በአብዛኛው ፖለቲካዊ ይዘት የጎላባቸው፣ “አገር አፍራሽና ደም አፋሳሽ ስብከቶችና ትንታኔዎች” እየተነገሩ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

በመንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚስተዋሉ በደሎችንና ኢፍትሐዊነቶች ሁሉ እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ መጣር፣ አጥፊዎችም ከስህተታቸው እንዲታረሙ በፍቅር መገሰፅ ሃይማኖታዊና የተለመደ አሠራር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገብል ሲል ገልጿል።

ስብከቶቹና ንግግሮቹ ፖለቲካውና ፖለቲከኞችን የሚተቹ ወይም የሚደግፉ ከመሆናቸው በላይ አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ የመቀስቀስና የማነሳሳት አዝማሚያ የሚታይባቸው መሆኑ ጉዳዩ ከየትኛው ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ጋር የማይስማማና ድጋፍም የሌለው ነው ሲል ኮንኗል።

የስብከት ልምምዱ አደገኛና በእጅጉ አሳሳቢ እንዲሆን ያደርገዋል ብሏል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ስብከትና አካሄድም የሰላም፣ የመከባበርና የአብሮነት ዕሴቱን የሚጎዳ በመሆኑ በአፋጣኝ ሊታረም ይገባል ያለው መግለጫው የሃይማኖት ተቋማትም እንዲህ ዓይነት ስብከት የሚሠብኩና የሚናገሩ አባቶችን፣ አስተማሪዎችን ወይም ሰባኪ አገልገዮችን እንዲታረሙ የማድረግ ተቋማዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button