ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ ተ.መ.ድ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ስደተኞችን ማስፈታቱን አስታወቀ፤ በርካታ ስደተኞችም ወደ አዲስ መጠለያ ጣቢያ እየገቡ መሆኑ ተገልጿል

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 23/ 2016 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ በዘፈቀደ እስር ላይ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መፈታታቸውና በአማራ ክልል 3,000 የሚሆኑ የሱዳን ስደተኞች ወደ አዲስ መጠለያ መዘዋወራቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽር በአዲስ አበባ 879 ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ያቀረቧቸውን አስተያየቶች እና ቅሬታዎች መሠረት በማድረግ እና ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ጋራ በመተባበር ችግሮቻቸውን ለመፍታት ባደረገው ጥረት እስረኞችን ማስፈታቱን ገለጿል።

ስደተኞቹ ከየት አገር እንደመጡ እና ለምን ያህል ጊዜ በእስር ላይ እንደቆዩ ድርጅቱ አልገለጽም።የችግሮቹ መንሥኤ ስደተኞቹ ተመዝገበው እውቅና አለማግኝታቸው መሆኑን የስደተኞችን ጉዳይ በመከታተል ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በዚህ ምክንያት በከተማ የሚኖሩ ስደተኞች በከፍተኛ ሁኔታ ለእስር ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሰው ኮሚሽኑ ከ120 በላይ እስረኞችን ማስለቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ስደተኞች አብዛኛውን ቁጥር ኤርትራውያን ይሸፍናሉ የተባለ ሲሆን ለእስር በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጫ መሆናቸውንም አክለዋል።

ዩኤንኤቺሲአር በሶስት ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በዓለምዋጭ እና በጾሬ፣ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከ7ሺሕ 426 በላይ ስደተኞች “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ካርድ እንደተሰጣቸው አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ በአማራ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች የምዘገባ ማረጋገጫው የተሰጣቸው እንዳሉ ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ እንደ ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ገለጻ፤ የምዝገባ ሂደቱ በዋናነት በመጠለያ ካምፖች ላይ የተወሰነ መሆኑ በከተማ የሚገኙ ስደተኞችን ለአደጋ ተጋላጭ ማድረጉን አንስተዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተያያዘ ዜና የኩመር እና አውላላ ካምፖች በፀጥታ ችግር ምክንያት መዘጋታቸውን ተከትሎ 3,000 የሚጠጉ ሱዳናውያን ስደተኞች አፍጥጥ ወደተባለው ቦታ መዘዋወራቸው ዩ.ኤን.ኤች.ሲ አር አስታውቋል።

እስከ 12,500 ግለሰቦችን የማስተናገድ አቅም ያለው የአፍጥጥ መጠለያ ጣቢያ በአከባቢው ያለው ከባድ ዝናብ ተግዳሮት ቢፈጥርበትም፣ በጸጥታ ቁጥጥር ዙርያ ግን አመርቂ ርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገልጿል።

ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እና አጋሮቹ ስደተኞቹ መሰረታዊ አገልግሎት በሚያገኙበት ዙርያ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም በነሐሴ 7/2016ዓ.ም. በአውላላ እና ኩመር የሚገኙ ስደተኞች ለሶስት ወራት ያህል በጸጥታ ችግር እና በአገልግሎት እጥረት ምክንያት ከመጠለያ ጣቢያዎቹ ወጥተው ኑሯቸውን በጎዳና ዳር አድርገው እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button