ዜናፖለቲካህግ እና ፍትህ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ከአዋሽ አርባ ወደ አዲስ አበባ የተዘዋወሩት ፖለቲከኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ አቀረቡ

አዲስ አበባ ሰኔ 6/ 2016 ዓ/ም፦ ህዳር 30 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ አዋሽ አርባ የወታደራዊ ካምፕ እስር ላይ ቆይተው ወደ አዲስ አበባ ከተዘዋወሩት ተጠርጣሪዎች መካከል ዘጠኙ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ “ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ አቀረቡ።

“ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ፖለቲካኞች “በሁከት እና በብጥብጥ በተለያዩ ነገሮች ላይ በመሳተፍ ህገ መንግስታዊ ስረዓቱን ለመናድ” የተጠረጠሩ ሲሆን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ዶቼ ቬሌ ዘግቧል። 

ከሰልፉ ጋር በተያያዘ የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ እና ጠበቃ አበራን ጨምሮ በአዋሽ አርባ ታሥረው የነበሩ 17 ሰዎች፣ አርብ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ. ም ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሠራቸው ይታወሳል።

ባለፈው ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት ተጠርጣሪዎቹ በዕለቱ  ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የ 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁን ተከትሎ ነው ፍርድ ብቱ ብይን ለመስጠት ለትናንት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።

ይህ በእንዲ እያለ የተፈጻሚነት የጊዜ ወሰኑ ባለፈው ሳምንት ካበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች፤ “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። 

አቤቱታውን በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል

ጋዜጠኞቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” በማድረጉ መሆኑን ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ ተናግረዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሶስቱ ጋዜጠኞች “ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዛቸው”፣ ከተያዙም በኋላ “በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲኖርባቸው” ይህንን መብታቸውን መነፈጋቸውን ጠበቃው ገልጸዋል።

የሶስቱ ጋዜጠኞች ጠበቆች ለፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ የፍትሐ ብሔር ችሎት ባቀረቡት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ላይ በተከሳሽነት የጠቀሱት የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮን ነው። 

ነሐሴ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ታሥረው የቆዩ ከ 80 በላይ ሰዎች ባለፈው ሳምንት  ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ባሰለፍነው ሳምንት ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ 52 ተከሳሾች ቅሬታ እና የክስ መቃወሚያ ለፍርድ ቤት አቅርበዋልአስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button