ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን የፖለቲካ ተልዕኮ ሰጥቶ ያቋቋመው ቡድን የስራ ግዜ እንዲጠናቀቅ የሀገሪቱ መንግስት ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/2016 ዓ.ም፡- የሱዳን መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሀገሪቱ ያሰማራው የፖለቲካ ተልዕኮ በአፋጣኝ እንዲያበቃ በይፋዊ ደብዳቤ ጠየቀ፤ ተልዕኮው የተቀመጠለትን አላማ ሊያሳካ አልቻለም ሲል የሀገሪቱ መንግስት በምክንያትነት አስቀምጧል።

አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው የሱዳን መንግስት ለጸጥታው ምክር ቤት የጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው የሀገሪቱ መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትም ሆነ ከዋና ጸሃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ገንቢ ግንኙነት ለመመስረት ቁርጠኛ ነን ብሏል።

በሱዳን በ2011 ታህሳስ ወር የተፈጠረውን አብዮት ተከትሎ በ2013 ዓ.ም የተቋቋመውን የሽግግር መንግስት ለማገዝ ተብሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 400 አባላት ያሉት የተልዕኮ ቡድን እንዲመሰረት ተደርጓል።

በሱዳን መንግስት ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ ሳዲቅ ተጽፎ ለአንቶኒዮ ጉተሬዝ የተላከው ደብዳቤ እንደሚያትተው በመንግስታቱ ድርጅት አማካኝነት የሱዳንን የሽግግር ሂደት እንዲያግዝ ተልዕኮ ተሰጥቶት የተቋቋመው ልዑኩ አላማውን በአጥጋቢ መልክ ሊያሳካ አለመቻሉን ጠቁሟል።

በሱዳን ወታደራዊ ሀይሉ መሪ አብዱል ፈታህ አልቡርሃን እና በፈጥኖ ደራሹ ሀይል መካከል ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ በሱዳን መንግስት እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል የነበረው ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ ይታወቃል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button