ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ግብረ-ኃይሉ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔን ጨምሮ ሃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27/2016 .ም፡ 37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም በጥር ወር የሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጊያለሁ ሲል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ለብዙሃን መገናኛ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከቅድመ ዝግጅቱ በተጨማሪ ስምሪት ወስዶ ወደ ስራ መግባቱን ግብረ ሀይሉ ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

ወቅቱ የገና እና የጥምቀት በዓላት የሚከበሩበት እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚካሄድበት በመሆኑ የሀገሪቱን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚያስችል ዕቅድ እየተመራሁ ነው ብሏል።

በአዲስ አበባ የፀጥታ አካላት ባካሄዱት የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለህብረተሰቡ ስጋት የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶችን በከፍተኛ ደረጃ መቆጣጠር የሚያስችል ስራ መስራቱን በአብነት አስቀምጧል።

በቀጣይ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔን ጨምሮ ሀይማኖታዊና መንግሥታዊ ሁነቶች በሰላም ተጀምረው በሰላም እንዲጠናቀቁ የህብረተሰቡን ድጋፍ ጠይቋል።

ኢትዮጵያ በጉባዔው የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችን እና እንግዶችን ተቀብላ ስታስተናግድ በተሰጣት ኃላፊነት እና በተጣለባትን እምነት የሚመጥን በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button