ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ቋሚ ኮሚቴው ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ድረስ በመሄድ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጎብኝቻለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4/2016 ዓ.ም፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌደራል ማረሚያ ቤት በህግ ጥላ ስር የሚገኙ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤት አባል የነበሩ እና ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በማቆያ ስፍራ የሚገኙ ግለሰቦችን አያያዝ መመልከቱን አስታወቀ።

ቋሚ ኮሚቴው የተመለከታቸው በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አቶ ክርስቲያን ታደለን እና በቂሊንጦ የሚገኘው የቀጠሮ ማረፊያ አቶ ጫላ ዋቶ (ዶ/ር ) ናቸው።

ስለማረሚያ ቤቱ አጠቃላይ አያያዝ ሁኔታ በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እጸገነት እና ሌሎችም አባላት የተጠየቁት አቶ ክርስቲያን ታደለ አዋሽ አርባ ከነበረው አያያዝ የተሻለ መሆኑን ገልጸው የአዋሽ አርባ ማቆያ ሊታይ ይገባል ብለዋል።

አሁን ባሉበት ማቆያ የቤተሰብ ጥየቃ ሰአት ከ6 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት መሆኑንና እንደ አስፈላጊነቱ መሻሻል ቢችል ሲሉ መጠየቃቸውም ታውቋል።

በቂሊንጦ በሚገኘው የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል የሚገኙት አቶ ጫላ ዋቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው አጠቃላይ አያያዙ ጥሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በአንድ ክፍል ውስጥ በርካታ ግለሰቦች እንደሚገኙና የአልጋ እጥረት እንዳለ ገልጸዋል፤ የተለየ ነገር እንዳላጋጠማቸው ገልጸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ መብዛትና መርዘም መኖሩንና ሊስተካከል ይገባል ብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ የቤተሰብ ጥየቃ የሰአት ገደብ በሁሉም ማዕከሎች ወጥ መሆን እንዳለበት በመግለጽ በቂሊንጦ የሚገኘው የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል በአንድ ክፍል ውስጥ በርካታ ግለሰቦች የሚገኙ መሆኑ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም የተመለከታቸውን ጉዳዮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩበት ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ተክሉ ለታ ማረሚያ ቤቱ የሰብአዊ መብትና የመብት ጥበቃን እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝን መሰረት አድርጎ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ነገሮችን እንደሚያቀርቡ ጠቁመው አገልግሎት የሚሰጠውም ሰው በመሆናቸው ብቻ እንጂ ሌሎች ጉዳዮችን መሰረት ያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ተክሉ ለታ ማረሚያ ቤቱ የሰብአዊ መብትና የመብት ጥበቃን እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝን መሰረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በቂሊንጦ የሚገኘው የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ያለው መጨናነቅ የተፈጠረው በጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ ሸዋ ሮቢት መውሰድ ባለመቻሉ መሆኑን አስረድተው በቀጣይ መፍትሄ ለመስጠት እንደሚሰራ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button