ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌ ወረዳ ከ80 በላይ ዋቄፋና አማኞች ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም፡- የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ፖሊስ የአምልኮ ስርአት በመፈጸም ላይ በነበሩ የዋቄፈና አማኞች ላይ በወሰደው እርምጃ ከ80 በላይ የእምነቱ ተከታዮችን ማሰሩ ተገለጸ።

ፖሊስ እርምጃውን የወሰደው የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የእምነቱ ተከታዮች በባቢሌ ከተማ የግማሽ አመት ጉባኤ ከሳምንት በፊት ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም እያካሄዱ በነበረበት ወቅት መሆኑም ተጠቁሟል።

የእምነቱ ተከታዮች ድርጅት የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ለማ ባይ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ከታሰሩት መካከል 25ቱ የጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ሲሆኑ 54ቱ ደግሞ የእምነቱ ተከታዮች ናቸው።

ምእመናኑ ካለፈው አርብ ጀምሮ በባቢሌ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ ብለዋል።

“ በፖሊስ ቁጥጠር ስር ከዋሉት መካከል 54 የሚሆኑት መጀመሪያ ላይ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ነበር ለቀናት የታሰሩት፣ ከዚያም በኋላ ነው ወደ ባቢሌ የፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱት” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። “በእስር ላይ የሚገኙትን ለመጠየቅ የሄዱ ሶስት ሰዎችንም ፖሊስ አስሯቸዋል፤ በዚህም ነው አጠቃላይ የታሰሩት አማኞች ቁጥር 82 የሆነው፣ አብዘሃኛዎቹ ወጣቶች ናቸው” ብለዋል።

እንደ ኮሙዩኒኬሽን ሃላፊው ገለጻ፣ ከታሰሩት መካከል ዋቄፋና እምነት የምስራቅ ሐረርጌ ሃላፊ የሆኑት ታጂ መሀመድ፣ የአከባቢው የእምነቱ መሪዎች የሆኑት ራጂ በዳዳ እና አብዳታ ቦጋላ እንዲሁም የአከባቢው የእምነቱ መምህር ዛዉዴ ግርማ (ዶ/ር) ይገኙበታል።

ለእስር የተዳረጉት ምእመናኑ ላለፉት ቀናት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንም ለማ አሳውቀዋል፣ ያለምንም ምክንያት ነው ለእስር የተዳረጉት ሲሉ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አዲስ ስታንዳርድ በጉዳዩ ዙሪያ የባቢሌ ወረዳ የፖሊስ ኢንስፔክተሩን ታጁ መሃመድን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም። ሌሎች የባቢሌ ወረዳ ባለስልጣናትን እና የምስራቅ ሐረርጌ ሃላፊዎችንም በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጡበት ለማድረግ የተደረገውሙከራ ምላሽ ባለማግኘቱ አልተካተተም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button