ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በትግራይ በክልሉ ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ነው ያሉትን ግፍ የሚቃወም እና ጾታዊ ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም፡- በመቀለ ከተማ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 20016 ዓ.ም በክልሉ ሴቶች ላይ በመፈጸም ላይ ያለውን ግፍ በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

በሰልፉ ላይ እገታና ጾታዊ ጥቃት ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የጥቃቱ ሰለባዎች ፍትህ እንዲያገኙ ጥሪ ቀርቧል።

የሰልፉ አስተባበሪ ከሆኑት መካከል የሆነችው ሰምሃል ኪዱ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቀችው በተለያዩ ተፋላሚ ሀይሎች አመካኝነት የክልሉ ሴቶች በርካታ ጥቃቶችን ተቋቁመው እዚህ መድረሳቸውን ጠቁሟ አሁንም አስጊ ነገሮችን በመጋፈጥ ላይ ይገኛሉ ስትል ገልጻለች። “አሁን እየጠየቅን ያለነው የተነፈገን ፍትህ እንዲያበቃ ነው” ስትል ገልጻለች።

በሰልፉ ላይ የተሳተፈች ብርክቲ ሀይሉ የተባለች የከተማዋ ነዋሪ በበኩሏ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶች የአካላዊ እና ስነልቦናዊ ስቃይ እንዲያበቃ በአጽንኦት ጠይቃለች፤ ማህበረሰቡ ለሴቶች ከለላ እየሰጠ፣ መብታቸውን እያስጠበቀ አይደለም ስትል በመተቸት በክልሉ ሴቶች ላይ በመፈጸም ላይ ያለው ጥቃት ሊቆም ይገባል ስትል አሳስባለች።

ሰልፈኞቹ በመቀለ ከተማ በሚገኘው ሮማናት አደባባይ በመሰባሰብ ወደ ክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በማምራት ድምጻቸውን አሰምተዋል። በጽ/ቤቱ ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር መገናኘት ባይችሉም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ከሆኑት ሃዱሽ ተስፋ ጋር ተገናኝተው ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል።

ሃላፊው የሴቶች ጥቃት ለማስቆም የሚደረገውን ትግል እውቅና በመስጠት “እዚህ በመገኘት ጥቃቱን በማውገዝ  እንቅስቃሴ በማድረጋችሁ አሁንም ቀጣይነት ያለው ትግል ማድረግ እንደሚገባ በግልጽ ያሳየ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

በቅርቡ በክልሉ ሴቶች ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች እንደሚያወግዙ የገለጹት ሃላፊው ፍትህን በሚያከብር ማህበረሰብ ዘንድ እንዲህ አይነቱ ተግባር ቦታ የሌለው እና የሚያስወቅስ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

እንዲህ አይነቱን አሳሳቢ ችግር ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል፤ “ህግ እና ስርአት እንዲከበር አበክረን እንሰራለን፣ አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ እንሰራለን ብለዋል።

ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬሰኔ 18 ቀን በአዲግራት ከተማ የተካሄደ ሲሆን ሰልፈኞቹ በክልሉ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም አጥፊዎች ተጠያቂ እንዶኑ፣ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

የክልሉ ከንቲባ ሰለሞን ሀጎስ የሰልፈኞቹን ሀሳብ እንደሚደግፉ በመግለጽ ጥቃት ፈጻሚዎችን ኮንነዋል። የክልሉ አስተዳደር ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ፣ ሰላም እና ስርአት ለማሰከበር እንደሚሰራ አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button