ዜናፖለቲካ

ዜና: በፌደራል መንግስቱና በፓርቲው በተሰጠው እውቅና “በጌታቸው ረዳ የሚመራ የህወሓት ልዑክ ከኤርትራ ጋር ድርድር ያደርግ ነበር” - ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2/2017 ዓ.ም፡- የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በፓርቲው እውቅና በጌታቸው ረዳ የሚመራ የህወሓት ልዑክ ከኤርትራ ጋር ድርድር ያደርግ እንደነበር አስታወቁ።

በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ህወሓት ከፍተኛ ጥረት ያካሂድ ነበር፤ ከአለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች እና ከሀያላን ሀገራት መሪዎችም ጋር ይነጋገር ነበር ሲሉ ጠቁመዋል።

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ጋር በተደጋጋሚ በሰላማዊ አማራጮች ዙሪያ መክሬያለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በመግለጫቸው በፓርቲው ስራ አስፈጻሚ እና በማዕከላዊ ኮሚቴው ውሳኔ መሰረት ከሁሉም ጋር ሰላም መፍጠር አለብን የሚል ውሳኔ መወሰኑን ተከትሎ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ከኤርትራ ጋር ድርድር ያደርግ እንደነበር ጠቁመዋል።

አቶ ጌታቸው ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም ሪፖርት አቅርበዋል ሲሉ የተደመጡት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) “ጠ/ሚኒስትር አብይ ራሳቸው ‘ሻዕቢያ ከናንተ ጋር ከባድ ቅሬታ አለው፤ ራሳችሁ ተግባቡ’ ይሉን ነበር” ብለዋል።

ደብረፅዮን፤ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ደም አፋሳሹ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ የኤርትራ ባለሥልጣናት እና የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች በምን ጉዳይ ላይ እንደመከሩ በዝርዝር ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ልዑክ ከኤርትራ ባለሥልጣናት ጋር በተደጋጋሚ ውይይት ያደርግ እንደነበር የጠቀሱት ደብረፅዮን፣ ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር የተካሄደውን ግንኙነት ሌላ መልክ ለማስያዝ ሆነ ተብሎ “በነባር አመራሮች” የተካሄደ አስመስሎ ማቅረብ ትክክል አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሐወልቲ አደራሽ በተካሄደው የህወሓት 14ኛ ጉባኤ እንደማይሳተፉ ባሳወቁበት ወቅት የህወሓት “ከፍተኛ አመራሮች” ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር እየሠሩ ነው ሲሉም ወቀሳ ማቅረባቸው ይታወሳል።

‘ከኤርትራ መንግስት ጋር ሁነን የፌደራል መንግስቱን እንምታው የሚል ጉዳይ አልነበረም” ከመጀመሪያው ጀምሮ እንደዚያ አይነት ሃሳብም አልነበረንም ሲሉ የገለጹት ደብረፅዮን “ከአንዱ ጋር ወግነን አንዱን ምምታት የሚል ጉዳይ በፍጹም አናደርገውም ብለን ወስነናል” ብለዋል።

የህወሓት ሊቀ መንበር፤ በትግራይ እና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች የነበረው የፀጥታ ጉዳይ በውይይቱ የተፈታ መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች አብይ የሚባሉ ጉዳዮች ግን በፌዴራል መንግሥቱ መሪነት እንደሚፈቱ ገልፀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button