ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና: በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች እየተባባሱ ያሉት ከትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በተፈጠረ “የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት” ሳቢያ ነው - ኢሰመኮ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች በአሳሳቢ ሁኔታ መባባሳቸውን አስታውቆ መንግስት ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠየቀ።

ኢሰመኮ ዛሬ ነሃሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለውን የእገታ ተግባር ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስቆም ለሰዎች እገታ መነሻና አባባሽ ምክንያት የሆነውን የሰላም መደፍረስና የትጥቅ ግጭትን በዘላቂነት በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ጨምሮ ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው” ሲል አሳስቧል።

እገታዎቹ የተባባሱት በተለይም “በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች” ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት ሳቢያ ነው ሲል ጠቁሟል።

የኢሰመኮ አደረኩት ባለው ክትትልና ምርመራ ውጤት መሰረት ተባብሰው የቀጠሉት እገታዎች የሚፈጸሙት “ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖች እና በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች” መሆኑን አመላክቷል።

“አጋቾች ሰላማዊ ሰዎችን በአብዛኛው በጉዞ (ትራንስፖርት) ላይ እያሉ አንዳንዴም ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው አግተው ወዳልታወቀ ቦታ በመውሰድ ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ክፍያ ይጠይቃሉ” ሲል ገልጿል።

ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ በርካታ ታጋቾች ግድያን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንሰተፈጸመባቸው ጠቁሟል።

እገታው በአብዛኛው እንደ ገቢ ማስገኛ እየተወሰደ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመኮ “በተደጋጋሚ፣ በተንሰራፋና በተደራጀ መልኩ” እንደሚፈጸም አስታውቋል፤ “አልፎ አልፎም እንደ በቀል፣ ለፖለቲካ ዓላማ ወይም የታገተ ሌላ ሰውን ለማስለቀቅ በሚል በአጸፋ መልኩ የሚፈጸም መሆኑንም ጠቁሟል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢሰመኮ በሪፖርቱ “ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ አካባቢ የታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሁኔታ በአብነት ጠቅሷል፤ “ሪፖርቱን ይፋ እስካደረኩበት ዕለት ድረስ ስንት ተማሪዎች በእገታ ሥር እንደሚገኙ እንዲሁም ምን ያክሉ በተለያየ አግባብ እንደተለቀቁ ለማረጋገጥ አልቻልኩም” ብሏል።

ኢሰመኮ ለችግሩ መፍትሔ ቢሆን ብሎ ካስቀመጣቸው ምክረ ሀሳቦች መካከል መንግሥት በጸጥታ አካላቱ አባላት ብቻ ሳይሆን የታጠቁ ቡድኖችን ጭምር ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስድ የጠየቀበት ይገኝበታል።

በተለይም በተደጋጋሚ እገታ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎችእገታን ለመከላከል ውጤታማ የጥበቃና ቁጥጥር ሥራዎችን ያከናውን ሲል አሳስቧል።

የታጠቁ ኃይሎች ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች መርሖችንና ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ እና ከእገታ ድርጊቶች እንዲታቀቡ ሲልም ኢሰመኮ በመግለጫው አሳስቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button