ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: “ከኢትዮጵያ ጋር በተፈራረምነው የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰጡት አስተያየት ተቀባይነት የለውም” - ሶማሊላንድ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ አስመልክቶ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የሰጡት አስተያየት ፍጹም ተቀባይነት የለውም ሲል የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ተቸ።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባድር አብደላቲ በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ህገወጥ ነው፣ የሶማሊያ ግዛታዊ አንድነት እና ሉዐላዊነት ሲደፈር ዝም ብለን አናይም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ የባድር አብደላቲ ንግግር እጅግ እንዳሳዘነው ገልጾ ሶማሊላንድ የሞቃዲሾ አስተዳደር አካል ሁና አታውቅም፣ አትሆንምም፣ ሉዐላዊ ግዛት ነች፣ የራሳችን እድለ በራሳችን እ.አ.አ በ1991 አውጀናል ሲል አመላክቷል።

የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቱርክ አቻቸው ጋር በጋራ በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ያደረጉት ንግግር ትክክል ያልሆነ፣ አሳሳች፣ የህዝባችንን ሉዐላዊነት ያላገናዘበ ነው ያለው የሶማሊላንድ መግለጫ ሶማሊላንድ ለስምምነቱ ሰነድ ተፈጻሚነት አሁንም ቁርጠኛ ናት ብሏል።

የግብጽ መንግስት የሶማሊላንድ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነትን እንዲያከብር የጠየቀው መግለጫው ግብጽ ከኢነርጂ ጋር በተያያዘ ከሚያዋስኗት ሀገራት ጋር ያሉባትን ቀወሶች በመፍታት ዙሪያ ብታተኩር ይሻላታል ሲል ምክረ ሀሳቡን ሰንዝሯል።

በሌላ ዜና የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት በቀጣይ የፈረንጆቹ አመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውን እና በሱማሊያ የተሠማሩትን የህብረቱን ወታደሮችን በመተካት በአዲስ ተልዕኮ በሀገሪቱ ስለሚሰፍረው ጦር ሃላፊነትና ስምሪት የቀረበለትን ሰነድ አጽድቋል።

ከቀጣይ አመት 2025 ጀምሮ በሶማሊያ የሚሰፍረው ጦር “የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ” (African Union Support and Stabilization Mission – AUSSOM) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን አትሚስን ይተካል ተብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከአራት ወራት በኋላ አዲስ ተልዕኮ አንግቦ በሶማሊያ ለሚሰፍረው ጦር ግብጽ ወታደሮቿን ለመላክ ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት ቀዳሚ መሆኗን ዘገባዎች ጠቁመዋል። ከግብጽ በተጨማሪ ጂቡቲም ጦሯን ለመላክ ፈቃደኛከሆኑ እና ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ዘገባዎቹ አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button