ህግ እና ፍትህዜና

ዜና፡ የትግራይ መምህራን ማህበር በክልሉ የተፈጸመውን የመምህርት ብርክቲ ግድያን አወገዘ 

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10/ 2016 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል ሰሜናን ምዕራብ ዞን ሽረ እንደስላሴ ከተማ ነሃሴ 7 ቀን 2016 የተፈጥሮ ሳይንስ መምህርት በሆነችው ብርክቲ ተስፋማርያም ላይ የተፈጸመውን ግድያ የክልሉ መምህራን ማህበር አወገዘ። 

በሰቲት ሁመራ አፈወርቂ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የነበረችው ብርክቲ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅላ ከቤተሰቧ ጋር በሽረ ከተማ ትኖር እንደነበር ተገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ በተመለከተው የማህበሩ መግለጫ፤ “ወንጀለኞቹ የብርክቲ ባለቤት ቤት አለመኖሩን በማረጋገጥ ልጆቿ ፊት እንደገደሏት” ገልጿል። 

ማህበሩ የፌዴራል መንግስቱ እና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጉዳዩን እንዲመረመሩ እና ወንጀለኞቹን ተጠያቂ እንዲያደርጉ ጠይቋል። አክሎም በክልሉ የተፈናቀሉ ሰዎችን ደህንነት የማረጋገጥ አስፈላጊነትንም በዐጽንዖት ገልጿል። 

ከትግራይ ጦርነት በኋላ በክልሉ የጸጥታ ችግሮች እየተስፋፉ ሲሆን በርካታ እገታዎች፣ ዘረፋዎች እና ግድያ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ነው።

አዲስ ስታንዳርድ በመጋቢት ወር ታግታ ሰኔ 2016 ዓ.ም. የተገደለችው የ16 ዓመቷ ማህሌት ተኽላይን ጨምሮ በክልሉ አስጊ ደረጃ የደረሰውን የግድያ እና የእገታ ተግባር በቅርቡ ዘግቧል።

በቅርቡ 27 የሚደርሱ የትግራይ ሲቪክ ማህበራት በጋራ ባወጡት መግለጫ በአስራ አንድ ወራት ውስጥ 12 ሴቶች መገደላቸውን፣ 80 መደፈራቸውን፣ 10 መታገታቸውን፣ 178 የሚሆኑት የግድያ ሙከራ ሰለባ መሆናቸውን ገልጸዋል። የሲቪክ ማህበራቱ እነዚህን ወንጀሎች ለማስቆም ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለመኖሩ ምክንያት ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል ሲሉ ገልፀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሰኔ ወር በአዲግራት፣ መቀለ እና በሌሎች ከተሞችም በክልሉ እየተፈጸሙ ያሉ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም የሚጠይቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄዷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button