ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የትግራይ ተፋነቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ የዘገየው “በአማራ ክልል በኩል የተደረገው ዝግጁነት ዝቅተኛ በመሆኑ ነው” -  ጀነራል ታደሰ ወረደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ተፋነቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር የዘገየው “በአማራ ክልል በኩል የተደረገው ዝግጅት ዝቅተኛ በመሆኑ ነው” ሲሉ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላምና ጸጥታ ሴክሬተሪያት ሃላፊ ገለጹ።

ተፈናቃዮቹ በመጡባቸው አከባቢዎች “በህገወጥ መንገድ አዲስ ሰፋሪዎች እንዲሰፍሩ መደረጉ እና ታጣቂዎች መኖር” ለመዘግየቱ ከሰጧቸው ምክንያቶ ይገኝበታል።

ጀነራሉ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር ያልተሳካበት ዋነኛ ምክንያት “በእኛ በትግራይ በኩል አይደለም” ብለዋል። “የአማራ ክልል መንግስት ለማስፈጸም የነበረው ዝግጁነት ዝቅተኛ ስለነበረ” ነው ያሉት ጀነራሉ፣ “የተለያየ ምክንያት በመደርደር፣ የማጓተት ሁኔታዎች ታይተዋል፤ በዚህም ምክንያት ዘግይቷል” ሲሉ ተደምጠዋል።

የደቡብ ራያ ተፈናቃዮችን ግንቦት 30 ቀን፣ የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮቸን ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ወደ ቀያቸው የመመለስ ዕቅድ የወጣው በእኛ በኩል ብቻ ሳይሆን በጋራ ያወጣነው እቅድ ነው የነበረው ያሉት ሌተናል ጀነራል ታደሰ በአፍሪካ ፓናል የመጀመሪያ ግምገማ ላይ በዝርዝር የታየ እና የታቀደ ስራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዕቅዱ የፌደራል መንግስት የአማራ ክልል መንግስት እና የትግራይ ተወካዮች በጋራ ያወጡት ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

ባስቀመጥነው ቀን ለመመለስ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ያሉት ጀነራሉ ላለመሳካቱ ዋነኛው ምክንያት የአማራ ክልል ዝግጁነት ማነስ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም መጠናቀቁ በተገለጸው የፕሪቶርያ ስምምነት ተግባራዊነትን በገመገመው የአፍሪካ ህብረት ሁለተኛው መድረክ ላይ ከደቡባዊ ትግራይ እና ከጸለምት የተገኘውን ልምድ በመቀመር የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን በፍጥነት ለመመለስ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በመጀመሪያው ዙር ግምገማችን ወቅት በዋናነት መግባባት ላይ ከተደረሰባቸው ነጥቦች መካከል በደቡብ ራያ፣ ጸለምት እና ምዕራብ ትግራይ በአከባቢ የተመሰረቱ አስተዳደሮች ህገወጦች ናቸው መፍረስ አለባቸው የሚለው ነው ሲሉ የተደመጡት ጀነራሉ ሁለተኛው ደግሞ ከ2013 ዓ.ም ወዲህ በአከባቢው ትጥቅ የያዙ ሀይሎች ትጥቃቸውን እንዲያወርዱ የሚለው ነው፣ በተጨማሪ ከ2013 ዓ.ም ታጥቆ የነበረ በግሉም ይሁን በሌላ ምክንያት ከነትጥቁ ይቆያል ተልዕኮ ግን አይሰጠውም (እንደዜጋ ይኖራል) የሚል ስምምነት ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

የአከባቢውን ጸጥታ በተመለከተ ደግሞ መካለከያ ይይዘዋል የሚል እንደነበር አውስተዋል።

በተጨማሪም ሌተናል ጀነራል ታደሰ “የትግራይ ግዛታዊ አንድነት በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት እየተሰራ ነው፣ በቅርቡ ከወራሪ ነጻ የሆነች ትግራይ የምናይ ይሆናል” ሲሉ መናገራቸውን ከትግራይ ቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሰያል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button