ቢዝነስዜና

ዜና፡ የእንግሊዙ ከፊ ጎልድ ኩባንያ በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን አስጀመረ

አበባ አበባ፣ ነሀሴ 15/ 2016 ዓ/ም፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆነውን የቱሉ ካፒ ወርቅ ፕሮጀክት ድርሻን በባለቤትነት የያዘው የእንግሊዙ ከፊ ጎልድ ኩባንያ አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ማስጀመሩን አስታውቋል።

ኩባንያው የሰራተኞች ካምፕ ግንባታን ጨምሮ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና በአቅራቢያ የሚገኝ የኩባንያውን አየር ማረፊያ የማሻሻል ስራ አስጀምሯል።

ኩባንያው እነዚህ ልማቶች ፕሮጀክቱን ወደ ፊት ለማራመድ የሚያስችሉ ወሳኝ እርምጃዎች መሆናቸውን አስታውቋል።

ከፊ ጎልድ በነሐሴ 14/2016ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በቱሉ ካፒ ማዕድን ማውጫ የመጀመሪያ ደረጃ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፤ አክሎም አስፈላጊ የሆኑ የፋይናንስ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ የፕሮጀክቱን ይፋዊ ጅምር በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

እንደ ኩባንያው ገለጻ ዋና ዋና ተቋራጮች ከዓለምአቀፍ አምራቾች ጋር በመተባበር አጠቃላይ የመሰረተ ልማት በጀቱን እየገመገሙ ሲሆን፤ ይህም ቋሚ የግንባታ ዋጋ ተመንን ለማረጋገጥ የሚረዳው ስምምነት በሚቀጥለው ወር ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ኩባንያው የማምረት አቅሙን ቢያንስ በ20 በመቶ ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥናቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

የማስፋፊያ እቅዱም ቀደም ሲል ከተቋቋሙ የጉድጓድ ስራዎች ጎን ለጎን የከርሰ ምድር ማዕድን ልማትን እንደሚጨምር ተገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኩባንያው የመጀመሪያ አበዳሪው የብድር ፈቃድ ማጽደቁን ተከትሎ በመስከረም ወር ውስጥ ከሁለተኛው ተባባሪ አበዳሪ ጋር የመጨረሻውን የብድር ፍቃድ ለማመቻቸት ያለመ የጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ገልጿል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሃሪ አናግኖስታራስ-አዳምስ በበኩላቸው፣ “ከፊ ጎልድ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዲሰራ በተፈቀደለት መሰረት በፍጥነት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።” ያሉ ሲሆን፤ አክለውም የአከባቢው አየር ንብረት ለማዕድን ስራው አዋ መሆኑንና ከመንግሥት እንዲሁም ከግል የጽጥታ እና ደህንነት ተቋማት ጋር በመተባበር ሥራው እየተቀላጠፈ እንደሚገኝ አንስተዋል።

ኩባንያው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እና የወርቅ ዋጋ በአንድ ወቄት 2,500 ዶላር መድረሱን ገልጿል።

ከፊ ጎልድ በቱሉ ካፒ የመጀመሪያው ሙሉ አመት ምርት 196 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም የፕሮጀክቱን ዕዳ ለመክፈል በቂ ነው ተብሏል።

የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ከአይራ ጉሊሶ ከተማ በስተምስራቅ 28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button