ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ምክር ቤት የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን አጸደቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም፡-የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ፓርላማ ከበርካታ ምክክር በኋላ የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ማጽደቁ ተገለጸ።

የፍትህ እና ህገ መንግስት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ሩበን ማዶል ምክር ቤቱ ስምምነቱን እንዲያጸድቀው ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ቢያቀርቡም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ምክክሮች ምክንያት ስምምነቱን ብሔራዊ ምክር ቤቱ አለማጽደቁን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው አስታውቀዋል።

ከሰባት ወራት በኋላ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ የሀገሪቱ የውሃ ሀብትና መስኖ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋትሉክ ሪክ ጃክ በስምምነቱ ላይ የኮሚቴዎችን ሪፖርት ማቅረባቸውን የጠቆሙት ዘገባዎቹ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ስምምነቱን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ሱዳን ፖስት ድረገጽ በዘገባው አመላክቷል።

“የፓርላማ አባላቱ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ስጦታ ይሆን ዘንድ ስምምነቱን እንዲጸድቅ እና ተፈጻሚ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ወስነዋል፤ እንዴት ስጦታ ይሆናል ከተባለ በስምምነቱ መጽደቅ ደቡብ ሱዳን በነጻነት የናይል ወንዝን በመጠቀም የመሠረተ ልማት ልማቷን ለመጀመር ያስችላታልና” ሲሉ የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ኦሊቨር ሞሪ ገልጸዋል ብሏል።

ቃል አቀባዩ ሞሪ የስምምነቱ ማፅደቁ ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝን በመጠቀም ሀይል ማመንጨትን ጨምሮ የወንዙን ሀብቶች ለመጠቀም የተሻለ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ ያደርጋታል ሲሉ መግለጻቸውንም አካቷል።

“ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ብሩህ ተስፋ ይሆናል፤ የስምምነቱ መጽደቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቆራረጠ የሚያማርረንን ኤሌክትሪክ ማመንጫን ጨምሮ ሀገሪቱ ተጠቃሚ የምትሆንበትን ሀብት ከወንዙ ለማግኘት የሚያስችል ነው ማለታቸውንም ዘገባው አስታውቋል።

ማዕቀፉን ግብጽ እና ሱዳን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቃወሙት ሲሆን፣ የቅኝ ግዛት ስምምነቱ በማስጠበቅ ኢፍትሐዊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ስለሚያስችላቸው ነው የሚል ትችት እየቀረበባቸው ይገኛል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button