ማህበራዊ ጉዳይርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕስ አንቀጽ: የፀጥታ ተቋማት ለገንዘብ ሲባል የሚደረግን እገታ ማስቆም አለመቻል ብሔራዊ ቀውስ ነው፤ እርምጃ የመውሳጃ ጊዜው አሁን ነው! 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12/ 2016 ዓ/ም፦ በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንት ኢትዮጵያውያን የሰሙት ዜና እጅግ የሚረብሽ ነው። ዜናው ከ150 በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮምያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ በታጣቂዎች መታገታቸውን የሚገልጽ ነው። ተማሪዎቹ በአማራ ክልል ከሚገኘው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ እያለ ነበር በታጣቂዎች የታገቱት።

አዲስ ስታንዳርድን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሃን የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር ያቀረቡት ዘገባ እንደሚያሳየው ወንጀሉ በተፈጸመ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ነበር አጋቾቹ ተማሪዎቹን ለማስለቀቀ ከፍተኛ ገንዘብ የጠየቁት። ኑሮአቸውን ለማሸነፍ የሚቸገሩ ድሃ ቤተሰቦች ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ለወንጀለኞች ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉት።

የፀጥታ ተቋማት ለገንዘብ ሲባል የሚደረግን እገታ ማስቆም አለመቻል ብሔራዊ ቀውስ ነው፤ እርምጃ የመውሳጃ ጊዜው አሁን ነው! 

በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የበርካታ ቤተሰቦችን ህይወት እያፈራረሰ እና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው አሰቃቂ ወንጀል ቀጣይ ሰለባ እኔ እሆንን እያሉ በሰቀቀን እየኖሩ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው።

ወንጀለኞች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ኢላማ ሲያደርጉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም በምዕራብ ኦሮምያ በሚገኘው የደንቢደሎ የዩኒቨርስቲ በርካታ ሴት ተማሪዎች ታገቱ የሚለው ዜና ሲሰማ በወቅቱ ብዙዎችን ያስደነገጠ ብሔራዊ አጀንዳ ሁኖ የነበር ሲሆን አሁንም ያልተቋጨ አጀንዳ ነው። የዚህ አይነት ለመቁጠር የሚያታክት የእገታ ታሪኮችን በበርካታ የሀገሪቱ ክልሎች መስማት የተለመደ ሁኗል። በዋናነት በኦሮምያ ክልል እንዲሁም በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ትግራይ እና ጋምቤላ ክልሎች እገታወች ተፈጽመዋል።

በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የበርካታ ቤተሰቦችን ህይወት እያፈራረሰ እና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው አሰቃቂ ወንጀል ቀጣይ ሰለባ እኔ እሆንን እያሉ በሰቀቀን እየኖሩ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው።

ከዚህ ባሻገር አዝማሚያው የሚያሳየው የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ያረጋግጣሉ ተብሎ የሚታመነው በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ግልጽ እና ይቅር በማይባል ደረጃ ውድቀት ላይ መሆናቸውን ነው። ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊትን ጨምሮ በተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች ላይ የማሻሻያ እና ማዘመኛ ተግባራት እየተከናወኑ ነው በሚል በመንግስት በኩል ቢገለጽም አሁንም ሀገሪቱ ላይ እየተባባሰ የመጣውን ችግር ለመፍታት ብዙ ስራዎች ይቀራሉ። ይህም በመልካም አስተዳደር፣ ህግ ማስከበር እና የተረጋጋ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ብዙ እንደሚቀር አመላካች ነው።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ስለዚህ ለገንዘብ ሲባል የሚደረግ እገታ የወንጀል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ የስርአት ችግር/ውድቀት ለመኖሩ ማሳያ ነው።  የህግ አስከባሪ አካላት በተቻላቸው መጠን ቀውሱን ከመፍታት ይልቅ ደንታ ቢስ እንሲሆኑ እና ተባባሪ እስከመሆን በሚያደርስ ሙስና እንዲዘፈቁ የሚያድግ ነው። 

ባለፉት ስድስት አመታት አዲስ ስታንዳርድን ጨምሮ በበርካታ መገናኛ ብዙሃን ቁጥር ስፍ የሌለው ዘገባዎች ከቀረቡ በኋላ አሁን ላይ ወንጀለኞች ተይዘው ለህግ የመጠየቅ ዕድላቸው የለም በሚያስብል ደረጃ ጠባብ መሆኑን በሚያሳብቅ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ግልጽ ወጥቷል። ይህም በርካታ ተዋናዮች እንዲቀላቀሉ የሚያበረታታ እና አስከፊ የጥቃት እና የዝርፊያ አዙሪት እየፈጠረ ይገኛል።

በመንግስት አካላት ቃል የሚገባው እና መሬት ላይ ያለው እውነታ መካከል ያለው ልዩነት መስፋት ዋነኛ ተግባራቸው የህብረተሰቡን ደህንነት እና ሰላም ማስጠበቅ በሆነው በጸጥታ ተቋማት እና በህዝቡ ዘንድ ያለውን መተማመን እየሸረሸረው ይገኛል። የእምነት መሸርሸሩ ደግሞ ለወንጀለኞች የተመቻቸ ሁኔታ ከመፍጠር ባለፈ ወንጀሉ እንደትርፋማ ልሙድ ተግባር እንዲቆጠር እያደረገው ይገኛል።

በሁለቱ የሀገሪቱ ትላልቅ ክልሎች ማለትም በኦሮምያ እና አማራ በመካሄድ ላይ ያሉ በርካታ ግጭቶችን ጨምሮ ለወንጀል ድርጊቱ መስፋፋት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ምክንያቶች መሆናቸውን መጥቀስ ይቻላል። ነገር ግን የችግሩ ዋነኛው መንስዔ የሀገሪቱ የፖለቲካ እና የደህንነት አመራሮች ቀውሱ ላለበት አሁናዊ አሳሳቢ ደረጃ እውቅና መንፈጋቸው ነው።

የጸጥታ ተቋማቱ ውጤታማ እንዲሆኑ ከሚያስፈልጉ፣ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ፖሊሲዎች እና ውጤታማ የህግ ማስከበሪያ ስትራቴጂዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ በምትካቸው ተቋማቱን የገዘፈ ምስል እንዲያገኙ እና የተቀናጀ የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲላበሱ እየተደረገ ይገኛል። ከአመት አመት የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናት ይህንን ወንጀል ለመከላከል ቃል ሲገቡ ቢደመጥም ተጨባጭ ውጤቱች ግን ሊታዩ አልቻሉም።

በመንግስት አካላት ቃል የሚገባው እና መሬት ላይ ያለው እውነታ መካከል ያለው ልዩነት መስፋት ዋነኛ ተግባራቸው የህብረተሰቡን ደህንነት እና ሰላም ማስጠበቅ በሆነው በጸጥታ ተቋማት እና በህዝቡ ዘንድ ያለውን መተማመን እየሸረሸረው ይገኛል። የእምነት መሸርሸሩ ደግሞ ለወንጀለኞች የተመቻቸ ሁኔታ ከመፍጠር ባለፈ ወንጀሉ እንደትርፋማ ልሙድ ተግባር እንዲቆጠር እያደረገው ይገኛል።

ለገንዘብ ተብሎ የሚፈጸም እገታ የኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ብቻ አይደለም የሚያስከትለው። ለእገታው የሚከፈለው ገንዝብ ከሚያስከትለው ቀጥተኛ የፋይናንስ ቀውስ ባሻገር የሚፈጥረው ስጋት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ያዳክማል፣ የሸቀጦች እና የሰዎችን ነጻ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ያደርጋል፣ የአከባቢውን ኢንቨስትመንት ያዳክማል፣ ደህንነታቸውን የሚያሰጠብቅላቸው ሁኔታዎች እናገኛለን በሚል ወጣት ባለሙያዎች እና ሥራ ፈጣሪዎች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ የተማረ የሰው ሃይል ፍልሰትን ያባብሳል።  ለመግለጽ በሚያዳግት ደረጃ የማህበረሰቡን መዋቅር በማዳከም የሚፈጥረው የቀውስ አዙሪት ከፍተኛ ነው።

ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ለመቅረፍ አስቸኳይ፣ ሁሉን አቀፍ እና ዘርፈ ብዙ አካሄድ ያስፈልጋታል። በመጀመሪያ ደረጃ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ ያሉ የሕግ አስከባሪ አካላት የተራቀቀ መንገድ ወንጀሉን የሚፈጽሙ አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገንዝበው ቀውሱን እንደ ብሔራዊ ቀውስ በመመልከት የተለያዩ የጸጥታ ተቋማትን በማስተባበር የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠይቃል።

በጸጥታ መዋቅሮች የጸረ እገታ ክፍሎች መቋቋም አለባቸው። በተጨማሪም ከእገታ ጋር በተያያዘ ያሉ የህግ ማዕቀፎች ጥብቅ እንዲሆን ማድረግ፣ ወንጀለኞች ላይ ፈጣን እና ከባድ ቅጣት የሚያከናንቡ መሆን ይገባቸዋል።

በሁለተኛ ደረጃ በሀገር ደረጃ መረጃ መር ፖሊስ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆን አለበት። ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና የመረጃ ትንተናዎች እገታዎችን ለመተንበይ፣ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት እንዲውሉ መደረግ አለበት። ከአለም አቀፍ ኤጀንሲዎች ጋር ትብብር በመመስረት ድንበር ዘለል የእገታ ቀለበቶችን ለመበተን መጠቀም ይገባል።

በሶስተኛ ደረጃ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው። በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ የሚፈስባቸው የመንግስት እና ደጋፊዎቹ የሆኑ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም ማህበረሰቡን ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ዘመቻ   

በሚሊዮን በሚቆጠሩ የመንግስት እና ተያያዥነት ባላቸው የሚዲያ ተቋማት በኩል የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ማህበረሰቡን ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር ወንጀለኞችን ለመከላከል እና ለመያዝ የሚያስችል እውቀት እንዲያገኝ ያስችላል። የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ውጥኖች በህግ አስከባሪዎች እና በሚያገለግሉት ማህበረሰቦች መካከል መተማመንን እና ትብብርን ሊያጎለብት ይችላል፣ ይህም ለአጋቾች ያለቅጣት እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን ይህ  ግን በመጀመሪያ ደረጃ የፌደራል እና የክልል መንግስት የችግሮቹን ደረጃ እንዲገነዘቡ ይጠይቃል።

በመጨረሻም ድህነትን እና ስራ አጥነትን ጨምሮ የወንጀል መንስኤዎችን መፍታት አስፈላጊ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያን በርካታ ወታደራዊ ግጭቶችን በፖለቲካ እልባት ማስቆም አጣዳፊ ጉዳይ ነው።

ይህ እትም ሁሉንም ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በተለያዩ አጋጣሚዎች ተማጽኗል። መንግስት ለቤዛ ክፍያ ሲባል የሚፈጸም እገታን ማስቆም አለመቻሉ የፖሊሲ ውድቀት ብቻ ሳይሆን በግልጽ ከነዚህ ግጭቶች ጋር የተያያዘ ነው።

መንግስት የህዝቡን አመኔታ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን ለመላው የዜጎች ደህንነትና መረጋጋት ለማስከበር የገባውን ቃል ለመጠበቅ መስራት አለበት። የእርካታ እና እርምጃ ያለመውሰድ ጊዜ አልፏል። እርምጃ የምሰጃ ጊዜው አሁን ነው! አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button