ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ወንድም እና ሌሎች እስረኞች በአስቸኳይ ከአስር እንዲፈቱ ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30/ 2016 ዓ/ም፦ በቅርቡ የተገደሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ወንድም እና ከግድያው ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ 11 ሰዎች እንዲፈቱ አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ። 

የመንግስት ባለስልጣናት ከበቴ ኡርጌሳ ጋር በተያያዘ ክስ ሳይመሰረትባቸው ታስረው የሚገኙ ሰዎችን “በአስቸኳይ እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ተከትሎ ፖሊስ የበቴን ወንድም ሚሎ ኡርጌሳን ጨምሮ 13 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለጸው ሂዩማን ራይትስ ዎች አብዛኖቹ እስካሁን በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። 

“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የበቴን ወንድም እና ሌሎች ሰዎችን ክስ ሳይመሰረትባቸው አስረው ማቆየታቸው፤ መንግስት እውነቱን ከሚወጣ ይልቅ እውነታው እንዳይገለጥ መከላከል መምረጡን ያሳያል” ሲሉ  የሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር ገልጸዋል።

የበቴ ቀብር መፈጸሙን ተከትሎ የታሰሩት ወንድማቸው ሚሎ እና የቤተሰቡ የቅርብ ጓደኛ የሆኑት አቶ ኤባ በመቂ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ ነገር ግን ሌሎቹ እስረኞች የት እንደሚገኙ እንደማይታወቅ እና ተገቢ ላልሆነ አያያዝ እንደሚጋለጡ ገልጿል። 

በሰኔ ወር የመቂ ፍርድ ቤት አቶ ሚሎ እንዲፈቱ ወሳኔ ቢያስተላልፍም እስካሁን አለመፈታታቸው ተገልጿል። “የጸጥታ አካላት አቶ ሚሎ የት እንደሚገኙ እንደማያውቁ እና በዕነሱ አለመያዙን እየገለጹ ነው” ሲሉ ለጉዳይ ቀርበት ያለቸው ግለሰብ ለሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጸዋል። 

መንግስት የአቶ ባቴ ኡርጌሳ ግድያ ጉዳይ አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለወንጀል ምርመራው ዓለም አቀፍ እርዳታ መጠየቅ አለበት ሲልም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ደረጅቱ አስገንዝቧል።  አክለውም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው የሚገኙትን ሰዎች በአስቸኳይ መልቀቅ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይህ በእንዲህ እያለ ሌላኛው የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ አሚነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ እየተፈጸም ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመፍታት አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ትርጉም ያለው እርምጃ መውሰድ አለመቻላቸውን ገልጿል። 

አምነስቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባሳለፍነው አመት በአማራ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መበቶች ጥሰቶች መቀጠላቸውንና ግለሰቦችም ተጠያቂ አለመደረጋቸውን ገልጿል። አክሎም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፍትህ ሳያገኙ ቀርተዋል ብሏል። 

“የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ምርመራ መልሶ ማካሄድ እና በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ የሰብዓዊ እና የህዝብ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰሱ ወንጀሎችን ለመመርመር አስቸኳይ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው” ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ አሳስበዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button