ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ግብጽ የህዳሴ ግድቡን ውሃ ሙሌት “ሙሉ በሙሉ እንደማትቀበለው”ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 27/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ አምስተኛ ዙር የዉሃ ሙሌት ማከናወኗን ተከትሎ ግብጽ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጽጥታው ምክር ቤት በላከችው ደብዳቤ የግድቡን ውሃ አሞላል “የአንድ ወገን ፖሊሲ” ስትል በመግለጽ ”ሙሉ በሙሉ እንደማትቀበለው” ገለጸች።

በግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባዳረ አብዱላቲ የተፈረመው ደብዳቤው፤ የኢትዮጵያ ተግባር “የአለም አቀፍ ህግ መርህዎችን እና በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል የፈደረሰውን የመርሆች ስምምነትን የሚጥስ ነው” ብሏል። 

ደብዳቤው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በቅርቡ የግድቡ የኮንክሪት ግንባታ ማጠናቀቅን አስመልክቶ ያደረጉትን ንግግር በመጥቀስ “ተቀባይነት የለውም” ሲል ገልጿል።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አካሄድ “የቀጠናውን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል” እና “በቀጠናው አገራት መካከል ያለውን ትብብር ፍላጎት የሚቃረን” በማለት ስጋቱን ገልጿል።

ግብፅ የውሃ ሀብቷንና አገራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መሠረት “ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎችን” ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

የግብጽ መግለጫ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብር አሕመድ ህዳሴ ግድቡ በሚቀጥለው አመት እንደሚጠናቀቅ እና የግድቡ 3ኛ እና 4ኛ ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ የወጣ ነው። 

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የአባይ ወንዝ ውሃን በመያዝ የኮንክሪት ግንባታ መጠናቀቁን መግለጻቸው “በግብጽ ተቀባይነት የለውም” ሲል ተቀዋውሞን አሰምቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ግብጽ ይህን ያለችው ካይሮ እና ሞቃዲሹ የደረሱትን ወታደራዊ ስምምነት ተከትሎ በሶማሊያ የጦር መሳሪያዎችንና ወታደሮችን በማሰማራቷ ምክንያት በቀጠናው ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ስምምነት መፈራረሟ ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር ያላት መልካም ግኑኝነት ወደ ውጥረት መቀየሩም ይታወቃል።

ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግሥት “ቀጣናውን ለማተራመስ ከሚሹ የውጭ ኃይሎች ጋር እየሰራ ይገኛል” ሲል ከሷል። “ቀጠና ሲታመስ ዝም ብላ እንደማትመለከትም” ገልጻለች።

በቀጣዩ ከድህረ አትሚስ አወቃቀር ኢትዮጵያ ባትሳተፍበት እንኳን፤ “የሶማሊያ ችግር የአከባቢውን ጸጥታ ማደፍረስ የለበትም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ አሳሰበዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button