ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት 'ኢትዮጵያ ሆን ብላ ጎርፍ እንዲፈጠር ውሃ እየለቀቀች ነው' ሲሉ ከሰሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24/2017 ዓ/ም፦ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ኢትዮጵያ “በሶማሊያ ጎርፍ እንዲከሰት ሆን ብላ ከግድቦቿ ውሃ እየለቀቀች ነው” ሲሉ  ከሰሱ። 

ፕሬዝዳንቱ በሞቃዲሾ መስከረም 20፣ 2017 ዓ/ም ከዘኢኮኖሚስት ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ፤ በሶማሊያ በጎርፍ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን ፎቶግራፎች አቅርበው፤ ድርጊቱን ኢትዮጵያ ፈጸመዋለች ሲሉ ከሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ኢትዮጵያ በጋራ ድንበር አቅራቢያ “በጎሳ ለተመሰረቱ ለሶማሊያ ሚሊሻዎች ትጥቅ እያስተላለፈች ነው” ሲሉ ክስ አቅርበዋል። እነዚህ መሳሪያዎች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው “በአልሸባብ እጅ ሊወድቁ ይችላሉ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

አክለውም ኢትዮጵያ “የግብፅ ወታደሮች ስምሪትን እንዲቃወሙ በሶማሊያ ውስጥ ያሉ የጎሳ መሪዎችን እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እያበረታታች ነው” ሲሉም ከሰዋል። ይህም ከቀጠለ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የሶማሊያ ተወላጆች የሚያቀቡትን ቅሬታ ሶማሊያ እንደምታነሳ ገልጸዋል። 

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመችበት ከየካቲት ወር ጀምሮ፣ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ውስብስብ ሆኗል።

ግብፅ በቅርቡ ከባድ መሳሪያ እና የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን ያካተተ ሁለተኛ ዙር ወታደራዊ ድጋፍ ወደ ሶማሊያ መላኳ ሁኔታውን የበለጠ አወሳስቦታል። ይህ ድጋፍ ግብጽ እና ሶማሊያ የፈጸሙት የመከላከያ ስምምነት አካል ሲሆን ይህም በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ ስጋት አስከትሏል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button