ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የግብጹ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች ጋር የሶስትዮሽ ጉባዔ ለማድረግ አስመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/ 2017 ዓ/ም፦ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ  እና ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ ጋር የሶስትዮሽ ጉባኤ ለማድረግ አስመራ ገቡ።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገ/መስቀል በኤክስ ገጻቸው እንደገለጹት የግንጽ የብሄራዊ ደህንነት ሚንስትር፣ የፕሬዝዳንት ካብኔ ኃላፊ እና የውጭ ጉዳይ ምንስትርን ያካተተ የአልሲሲ ልዑክ ዛሬ ጠዋት አስመራ ገብተዋል።

ልዑክ ቡድኑ አስመራ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

በትላንትናው ዕለት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ ኢርትራ መግባታቸው እና ‘በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት’ ዙርያ ከኢሳያስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል። 

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገ/መስቀል የግብጽ እና የኤርትራ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማሻሻል እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ገልጸዋል። 

ይህንንም ተከትሎ  የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ፣ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ እና ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ የሶስቱን አገራት ግንኙነትን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጠናው ጸጥታ እና መረጋጋት ዙሪያ የሶስትዮች ጉባዔ ያደርጋሉ ተብሏል። 

የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሶማሊያ ማሰማራቷ ይታወቃል። ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው አካል ነው። በቅርቡም ግብጽ ሁለተኛ ዙር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ከባድ መሳሪያዎች እና ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች የጫነ የግብጽ ግዙፍ ወታደራዊ የጭነት መርከብ ወደ ሶማሊያ መላኳ በቀጠናው ላይ ከፍተኛ ውጥረት አስከትሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከዛ በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባህር በር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል። 

በትላንተናው ዕለት በኤርትራ እና በሶማሊያ መሪዎች መካከል “በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዋነኝነት በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ላይ ያተኮረ” ውይይት አድርገዋል

ሁለቱ መሪዎች “አስተማማኝ የመከላከያ እና የጸጥታ መዋቅርን ጨምሮ ጠንካራ እና ሉዓላዊ ተቋማትን መገንባት” አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button