ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በላሊበላ ከተማ በጸጥታ ስጋት ምክንያት 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25/ 2017 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት በላሊበላ ከተማ 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸውን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዲያቆን አዲሴ ሲሳይ በአከባቢው ባለው የጸጥታ ስጋት የተነሳ 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆማቸውንና ከ180 በላይ አስጎብኚዎች ከሥራ ውጭ እንደሆኑ መግለጻቸውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል

ኃላፊ አክለውም የቱርዚም ዘርፍ መቀዛቀዙ የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲዳከም ማድረጉን ገልጸዋል።

የላሊበላ ከተማ እና አከባቢዋ ቱሪስት አስጎብኝ ማኅበር ሰብሳቢ አቶ እስታሉ ቀለሙ በበኩላቸው ማኅበረሰቡ ቱሪዝምን ብቸኛ  መተዳደሪያዉ አድርጎ መቆየቱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ባለፉት አራት ዓመታት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ  በአካቢዉ በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል ባለ ግጭት  ቱሪስቶች ወደ ስፍራዉ ባለመምጣታቸዉ 200 የሚደርሱ የላሊበላና አካባቢዉ አስጎብኞች ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸውን ጠቁመዋል።

በማስጎብኘት ሥራ ላይ የተሰማሩት ዲያቆን ደስታው አበበ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም 25 ከሚደርሱ የቱሪስት አስጎብኞች ጋር ሲሰሩ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ላይ ሁሉም መዘጋታቸውን አመልክተዋል።

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከውጭና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች  ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ገቢው የተሰላው የውጭም ሆነ የየአገር ውስጥ ጎብኚዎች እንደ አካባቢው ሁኔታ በቀን ለመኝታ፣ ለመግብ ፣ለአስጎብኝ፣ ለጫማ ማስዋብና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያወጣው ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button