ዜናፖለቲካ

ዜና፡ መንግስት ስምምነቱን ተከትሎ “የኦነሠ ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ካምፕ እየገቡ ነው” አለ፤ የኦነሠ መረጃውን ወድቅ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25/ 2015 ዓ/ም፦ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መገንጠሉን ካስታወቀው በጃል ሰኚ ረጋሳ የሚመራው ቡድን ጋር የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተክትሎ በርካታ የታጠቁ አባላቱ ወደ ተዘጋጁ መዕከላት እየገቡ እንደሚገኝ ገለጸ።

የኦርሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ የሰላም ጥሪን የተቀበሉ ታጣቂዎች “ከጫካ ወደ ወደተዘጋጀላቸው የስልጠና ቦታ በመግባት ላይ መሆናቸውን” ገልጿል።

የክልሉ መንግስት የታጣቂ ቁጥር በይፋ ባይገልጽም የክልሉ ሚዲያ ኦቢኤን ምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደበረት፣ ጮቢ፣ ኢልፋታ፣ አና አምቦ፣ ሚዳቀኝ እና ጂባት ወረዳዎች የነበሩ ከ800 በላይ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪን በመቀበል መግባታቸውን ዘግቧል።

የሰላም ስምምነቱን የተፈራረሙ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ወደ ስልጣና ማዕከል እየገቡ መሆኑ መገለጹን ተከትሎ በጃል መሮ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ትናንት አመሻሹን ባወጣው መግለጫ “የተቀነባበረ ድራማ” ሲል ውድቅ አድርጎታል። ቡድን በመግለጫው “መንግስት እራሱ ያዘጋጃቸውን ታጣቂዎች ነው እያስገባ ያለው” ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የቀድሞ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል ባሳለፍነው እሁድ የተፈጸመው ስምምነት ይዘት እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

በመስከረም ወር ጃል ሰኝ ነጋሳ በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሳችንን አግልለናል ሲሉ ማሳወቃቸውን ይወሳል። ጃል ሰኝ ተለይተው የወጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ ድርጅቱ “መተዳደሪያ ህግ እና ደንብ” የሌለው ነው ሲሉም ገልጸው፤ መሪውን ጃል መሮን “አምባገነን” ሲሉ ጠርተዋል።

ጃል ሰኚ ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ጋር በነበራቸው ቆይታ “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መሪ ሆነው የተሾመው ግለሰብ የድርጅቱ ሕግ እርሱ ነው፤ ድምቡም እርሱ ነው፤ ድርጅቱም እርሱ ነው፤ ለዓመታት፣ የግል ፍላጎቱን ከድርጅታዊ መርሆች ጋር ለማስማማት ጥረት ሲደረግ ቢቆይም፣ ነገር ግን እነዚህ ሙከራዎች የበለጠ ውድቀትን ነው ያስከተሉት” ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በዚህም ምክንያት “በተለያዩ አካባቢዎች ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ኃይሎች ወደ ስርዓት አልበኝነት ተሸጋግ” ሲሉ ገልጸዋል።

ከመንግስት ጋርም የሰላም ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል።

ቡድኑ ከመንግስት ጋር ስምምነት ማድረጉን ተከትሎ በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጃል ሰኚ ከወራት በፊት “በስነምግባር ጉድለት መባረሩን” አስታውቋል። ስምምነቱም “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚመለከት አይደለም” ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button