አዲስ አበባ፣ ህዳር 27/ 2017 ዓ/ም፦ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈጸሙት የቀድሞው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራር ሰኚ ረጋሳ ከሁለት ቀናት በኋላ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ገለጹ።
ሰኚ ነጋሳ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ስምምነቱ በሰላም ጉዳዮች እና የታጣቂዎቹ ቀጣይ እጣ ፈንታ ላይ ትኩረት ማድረጉን ተናግረዋል።
አክለውም ከመንግስት ጋር የተደረገው ስምምነቱ 13 አንቀጾችን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰው አፈጻጸሙም በሰምምነቱ መሰረት ተግባራዊ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። ክትትል የሚደረግበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
“ለአመታት በኦሮሚያ ምድር የተደረገው ግጭት ሰላማዊ ሰዎችን ከመጉዳቱ በቀር ጥቅም ስለሌለው ለሀገሪቱ ሰላም ብለን መሳሪያችንን አዝቅዝቀን ከመንግስት ጋር ስምምነት አድርገናል” ያሉት ጃል ሰኚ መንግስትም ስምምነቱን “ለህዝቡ ሲል” ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የቀድሞ አመራሩ የስምምነቱን ይዘቶች በሙሉ ባይገልጹም በሰላም እና በመግባት ላይ ያሉት ታጣቂዎች እጣ ፈንታ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በግጭቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መተካት የሚቻልበት ሁኔታ በስምምነቱ ተካቷል ብለዋል።
አክለውም ሌሎች በጫካ ያሉ “የቡድን አባላትና የትግል ጓዶቻቸው ቆም ብለው የሕዝቡን ጉዳት በመመልከት እየቀረበ ያለውን የሠላም ጥሪ እንዲቀበሉ” ጠይቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ በስምምነቱ “ደስተኛ” መሆኑን ገልጾ “በጫካ የቀሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ” ጥሪ አቅርቧል።
የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መገንጠሉን ያስታወቀው በጃል ሰኚ ረጋሳ የሚመራው ቡድን ህዳር 23 ቀን 2017 የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። ስምምነቱን ተክትሎም በርካታ የታጠቁ አባላት ወደ ተዘጋጁ የስልጠና መዕከላት እየገቡ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
የክልሉ መንግስት የታጣቂ ቁጥር በይፋ ባይገልጽም የክልሉ ሚዲያ ኦቢኤን ምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደበረት፣ ጮቢ፣ ኢልፋታ፣ አና አምቦ፣ ሚዳቀኝ እና ጂባት ወረዳዎች የነበሩ ከ800 በላይ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪን በመቀበል መግባታቸውን ዘግቧል። አስ