ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷን ሲፒጄ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9/ 2017 ዓ/ም፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷንና በእስር ላይ ካሉ ስድስት ጋዜጠኞች መካከል አምስቱ የሞት ቅጣት ሊያስከትል የሚችል የ”ሽብርተኝነት” ክስ ተመስርቶባቸዋል ሲል የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ትናንት ሐሙስ ዕለት ይፋ ባደረገው የ2024 የጋዜጠኞች እስር ሪፖርት አስታውቋል።

ስድስተኛው ጋዜጠኛ ዬሺሃሳብ አበራ  በአማራ ክልል “ውጥረት እየተባባሰ” እና “የጅምላ እስራት” በተከሰተበው ወቅት ባለሥልጣናቱ “የሕግ የማስከበር ዘመቻ” በጠሩበት ወቅት በመስከረም 2024 መታሰሩን ገልጿል። ሲፒጄ ባለሥልጣናቱ የታሰረበትን ምክንያት  ወይም የቀረበበትን ክስ አለመግለጻቸውን አስታውቋል።

የእስር እርምጃዎቹ የተወሰዱት በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት ጋር የሚገጣጠም መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፤  ባለሥልጣናቱ “የጦር መሣሪያ የታጠቁ ቡድኖችን እና ደጋፊዎቻቸውን” ለማጥፋት በሚያደርጉት ዘመቻ “ሲቪሎችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ ምሁራንን እና ጋዜጠኞችን” ዒላማ አድርገዋል ብሏል።

ሲፒጄ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋዜጠኞችን ለማሰር “ብዙውን ጊዜ ግልጽ ያልሆኑ የሽብርተኝነት ወይም የጽንፈኝነት ክሶችን” ይጠቀማሉ።

በአፍሪካ ውስጥ እጅግ በከፋ ሁኔታ ህግ የማይከበርባት ሀገር  ኤርትራ ስትሆን ከፈረንጆቹ 2000 መጀመሪያ ጀምሮ 16 ጋዜጠኞች ያለ ምንም ክስ ታስረዋል ተብሏል። ካሜሩን እና ሩዋንዳ እያንዳንዳቸው አምስት ጋዜጠኞችን በማሰር የሚከተሉ ሲሆን በናይጄሪያ ደግሞ አራት እስረኞች ይገኛሉ።

በአለም አቀፍ ደረጃ ቻይና በ50 ጋዜጠኞች በማሰር ቀዳሚ ስትሆን እስራኤል 43 ጋዜጠኞችን፣ ምያንማር ደግሞ 35 ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ ሲፒጄ ሪፖርት እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2024 ድረስ ቢያንስ 361 ጋዜጠኞች በዓለም ዙሪያ ታስረዋል፤ ይህም ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው።

የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ በጎርጎሮሳውያኑ 2023 ባወጣው የጋዜጠኞች እስር ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ስምንት ጋዜጠኞችን በማሰር በአፍሪካ ሦስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጥጧታል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button