ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ 'ልዩ የፀጥታ ዘመቻ' መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27/ 2017 ዓ/ም፦ የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በማርሳቢት እና ኢሲዮሎ ግዛቶች በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ ‘ልዩ የፀጥታ ዘመቻ’ መጀመሩን አስታወቀ። 

አገልግሎቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚጠቀምባቸውን መሸሸጊያዎች ለቆ እንዲወጣ ለማድረግ “ኦንዶአ ጃንጊሊ ኦፖሬሽን” የተባለ ዘመቻ ከትናንት ጥር 26 ቀን ጀምሮ እንደሚያካሄድ ገልጿል።

በማርሳቢት ግዛት በተካሄደው የዘመቻ ማስጀመሪያ ላይ የፖሊስ አገልግሎች አስተዳደር ምክትል ኢኒስፔክተር ጄነራል ጊልበርት ማሴንጌሊ፣ የዲሲአይ ዳይሬክተር መሐመድ አየ አሚን እና ሌሎች የጸጥታ አዛዦች እና ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።

በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄደው ዘመቻ ለኬንያ ብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሚጥሉ ህገወጥ ስራዎችን በሚያከናውኑ ወንጀለኞች ላይ ያነጣጠረ ነው ነው ተብሏል። 

ይህም የወንጀል ድርጊት የጦር መሳሪያ፣ የአደንዛዥ ዕፅ እና የሰዎች ዝውውር፣ ህገወጥ የማዕድን ማውጫ፣ የጎሳ ግጭቶችን ማነሳሳት እና በተለይም በሶሎሎ፣ ሞያሌ፣ ሰሜን ሆር እና ሜርቲ ንዑስ ግዛቶች ውስጥ የቤዛ ክፍያ መጠየቅ የሚደረጉ እገታዎችን ያካትታል ሲል ገልጿል።

የፖሊስ አገልግሎች አስተዳደር ምክትል ኢኒስፔክተር ጄነራል ጊልበርት ማሴንጌሊ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ የአካባቢው ማህበረሰቦች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን አረጋግጠው እንዲረጋጉ እና በቦታው ካሉ የፀጥታ ቡድኖች ጋር እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ባሳለፍነው አመት ነሃሴ ወር  የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኬንያና ድንበር አካባቢ “ዜጎችን የማገት፤ ንብረት የመዝረፍ የማውደምና ህገወጥ ማዕድን የማውጣትና ማዘዋወር” ተግባራት እየፈጸመ መሆኑን እና ከሶማሊያው “አልሸባብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው” የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የመረጃ ተቋማት ማስታወቃቸው ይታወሳል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ተቋማቱ በወቅቱ ባደረጉት በውውይታቸው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር እና በኬኒያ ውስጥ “ዜጎችን የማገት፤ ንብረት የመዝረፍ የማውደምና እንዲሁም የሰዎችን እንቅስቃሴ የማስተጓጎል” ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። 

በተጨማሪም ቡድኑ “የኮንትሮባንድ ንግድ፤ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፤ ህገወጥ የማዕድን ማውጣትና ማዘዋወር” ስራዎች ላይ መሰማራቱንና ይህንንም ለማስቆም የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የመረጃ ተቋማት አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ተጠቁሟል።

“ሁለቱ የሽብር ቡድኖች” በአካባቢው እና በቀጣናው የደቀኑትን የሽብር ስጋት በጋራ ለመከላከልና ለመቀልበስ ይረዳ ዘንድ የተቀናጀ ኦፐሬሽን አጠናክረው ለመቀጠል መወሰናቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል፡፡

የሁለቱ ሀገራት አቻ የመረጃ ተቋማት የሳይበር ጥቃትን በጋራ ለመከላከል እንዲሁም የሀገራት አሁናዊ ስጋት እየሆነ ያለውን የስነ ልቦና ጦርነትንም ለመከላከል እና መልሶ ለማጥቃት በሚደረግ ጥረት በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተመልክቷል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button