ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እንዲስፋፋ፣ የፊስቱላ ተጠቂዎች ቁጥር እንዲሻቅብ አድርጓል - የክልሉ ጤና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም፡-በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እንዲስፋፋ ማድረጉ ተገለጸ፤ የጸጥታ ችግሩ የፊስቱላ ተጠቂ እናቶች ቁጥር እዲጨምር ማድረጉም ተጠቁሟል።

ከክልሉ ለተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የማኅበረሰብ መሪዎች በወቅታዊ የኤች አይቪ ኤድስ ሁኔታ እና ምላሽ ላይ የንቅናቄ መድረክ እና ሥልጠና ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ በየጊዜው እየተፈጠሩ ያሉ የጸጥታ ችግሮች የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እንዲስፋፋ እያደረጉ መኾኑ ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ሰብክት ጸሐፊ መላከ ብርሃን ፍስሃ ጥላሁን አሁን አሁን በወቅታዊ ጫና በተፈጠረው መዘናጋት ስለ ቫይረሱ የሚሰጠው ትምህርት ቀንሷል ብለዋል።

የባሕር ዳር ከተማ ዑለማ ምክር ቤት አባል ሼሕ ከድር መሐመድ ባለፉት ዓመታት የነበሩ የጸጥታ ችግሮች ለኤች አይቪ ኤድስ የነበረውን ትኩረት ቀንሶታል ብለዋል፡፡ አሁን ላይ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ደርሷል፤ በጋራ በመሥራት ሕይዎትን መታደግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ኤድስ ክትትል እና ግምገማ ባለሙያ መንግሥቱ መንገሻ በክልሉ ያለው የኤች አይቪ ስርጭት ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት የተፈጠሩ ግጭቶች እና መፈናቀሎች የኤች አይቪ ኤድሰ ስርጭት እንዲሰፋ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

በግጭት ወቅት አስገድዶ መደፈር እና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች እንደሚኖሩ የተናገሩት ባለሙያው እንዲህ ዓይነት ሂደቶች ስርጭቱ እንዲሰፋ እያደረጉ መኾኑንም አመላክተዋል፡፡

በግጭት ምክንያት ያቀዱት አልሳካ ሲል እና ሕይዎት አስቸጋሪ ስትኾን ሰዎች ተስፋ እንደሚቆርጡ እና ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡ በግጭት ምክንያት በሚኖረው መፈናቀል እና የኑሮ ደረጃ መቀነስ ላልተፈለገ ሥራ እንደሚያጋልጥም አንስተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በክልሉ የተፈጠሩ ተደጋጋሚ ግጭቶች እና ሌሎች ችግሮች በክልሉ የኤች አይቪ ስርጭት እንዲሰፋ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

በአማራ ክልል 175 ሺህ 955 ወገኖች በኤች አይ ቪ ኤድስ መያዛቸውን ጠቁመው በክልሉ የስርጭት ምጣኔ 1 ነጥብ 09 በመቶ ነው፤ ይኽም በጤና አጠራር ወረርሽኝ ነው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ 0 ነጥብ 9 ነው ተብሏል። የክልሉ ስርጭት ከሀገር አቀፉ እንደሚልቅም መግለጻቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታና የግንዛቤ ማነስ የፊስቱላ ችግር ያለባቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ማስታወቁን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ዘግቧል።

በአገር አቀፍ ደረጃ በፊስቱላ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 140 ሺህ ያደገ ሲሆን በአማራ ክልል ደግሞ እስከ 39 ሺህ ይደርሳል ተብሏል።

የፊስቱላ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ ለ9ነኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ በባህር ዳር ሲከበር የተገኙት በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች ጤና ክትትል ባለሙያ ዶ/ር ኤርሚያ አዱኛ በግንዛቤ እጥረትና ክልሉ አሁን ባለበት ወቅታ የፀጥታ ሁኔታ በአማራ ክልል የፊስቱላ ተጠቂ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button