እለታዊ ዜና፡ ግጭቶች እየተካሄዱ ባሉበት በአማራ ክልል መዲና ሊካሄድ የታቀደው 11ኛው ጣና ፎረም መራዘሙ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12/ 2016 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ከጥቅምት 2 እስከ 4 2016 ዓ.ም ድረስ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው 11ኛው ጠና ፎረም ወደ ሚያዝያ ወር መራዘሙ ተገለፀ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናቶች ተቋም ያዘጋጀው ፎረሙ የተራዘመው “ባልተጠበቁ ሁኔታዎች ምክንያት”  መሆኑን እና የጣና ቦርድና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጣና ሴክሬታሪያት የጋራ መግባባት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ጠና ፎረም የሚካሄድባት ባህርዳር ከተማን ጨምሮ በርካታ የአማራ ክልል ከተሞች በፌዴራል መንግስት እና ፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት አስተናግደዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተውጇል፡፡

በቅርቡም ከተሞቹ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ መሆኑ ቢስተዋልም በተለያዩ ከተሞች አደስ ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተሰምቷል፡፡ ከትላንት በስቲያም በላሊበላ ከተማ ተኩስ እና ከባድ መሳሪያ ድምፅ መሰማቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአህጉሩ ለሚስተዋሉ የደህንነት ጉዳዮች ላይ አፍሪካዊ መፍትሄ ለማፈላለግ በ2002 የተቋቋመ ጣና ፎረም በ2002 የተቋቋመው ጣና ፎረም ከ50 በላይ ተሳታፊዎችን በአንድ ላይ በማገናኘት ለተከታታይ ስምንት ዓመታት ውይይት ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡አስ

Exit mobile version