ዜና፡ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት “ጠንካራ ነው” ሲሉ የአሜሪካ አምባሳደር ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16/ 2016 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በቅርቡ “ሰብዓዊ መብቶችን እና ምክክሮችን የሚመለከት የፖሊሲ ንግግር” በሚል ርዕስ የሰጡትን መግለጫ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “የተሳሳተ” እና “መረጃ የጎደለው” ሲል መቃወሙን ተከትሎ አምባሳደሩ አሜሪካ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት “ጠንካራና መልካም” መሆኑን አረጋግጠዋል። 

ኤርቪን ማሲንጋ ግንቦት 14 ቀን ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ ነው ገልጸዋል። 

አምባሳደሩ “በትግራይ ጦርነት ወቅት አሜሪካ ከሰጠችው ትኩረት አንጻር አሁን በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ውስጥ ላለው አማራ ክልል የሰጠችው ያነሰ ነው” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ  ምልሽ ሰጥተዋል። 

“የአሜሪካ መንግስትም ሆነ አዚህ ያለነው ተወካዮች ሰለ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአኩል ደረጃ ያሳስበናል፤ በጦርነቱ ወቅት ግን የሰብዓዊ ድጋፍ መንገድ ይመቻች ብለን ስንሞግት የነበረው ለትግራይ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባአቸው አካባቢዎች በሙሉ ነው” ብለዋል። 

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት በተመለከተ አምባሳደሩ “እያደገ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለንግድ የሚሆን አስተማማኝ የባህር በር እንደሚያስፈለገው በሚገባ እንረዳለን፤ ለዚህም ኢትዮጵያ ከጅቡቲ፣ ኬንያ እና ከሌሎች አገራት ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር ስትጥር እንመለከታለን። ይህን ጉዳይ በቀጠና ደረጃ በቀጣይ ለመነጋገር እንዲቻል በይፋ አስታየት ከመስጠት አስፈላጊ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። 

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በአሜሪካን ግቢ በሰጡት መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና የፋኖ ታጣቂዎችን ጨምሮ በረካታ የታጠቁ ኃይሎች ከመንግስት ጋር እየተዋጉ መሆኑን ገልጸው ጊዜያዊ ሀገር አቀፍ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ያለምንም ፍርድ ግድያ፣ የዘፈቀደ ጅምላ እስር፣ እገታ፣ በግጭት ጋር የተያያዘ ጾታዊ ጥቃቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባፋጣኝ፣ ትኩረት ተሰጥቷቸው፣ ተጠያቂነትን ባሰፈነ መልኩ፣ እውነተኛ በሆነ ግልጽነት ባለው የሽግግር ፍትህ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ግንቦት 9፣ 2016 መግለጫ የሰጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤  የአምባሳደሩ መግለጫ “የተሳሳተ” እና “መረጃ የጎደለው”  ሲል ተቃውሟል።   በተጨማሪም “የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመምከር የሞከረ ነው” ሲልም ገልጿል፡፡

አምባሳደሩ ባደረጉት ንግግር “በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣን መንግስት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሃንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግስትን ያነሳ ነው” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስጋቱን ገልጿል።

የአምባሳደሩ መልዕክት ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ እንደሆነም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። አስ

Exit mobile version