ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ በክልሉ መንግስት ያለ ህግ አግባብ ሶስት አባላቱ መታሰራቸውን ገለፀ፤ በአሽቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23/ 2016 ዓ.ም፡- የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ የሲዳማ ክልል መንግስት ቤንሳ ወረዳ በዳዬ ከተማ ሶስት አባላቱን ያለ ህግ አግባብ ማሰሩን ገለፀ። የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገነነ ሃሳና ለአዲስ ስታንዳርድ፣ አለማየሁ አየለ፣ ሀብታሙ ታሪኩ እና ጌታሁን ገናሌ የተባሉ አባላት ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ መታሰራቸውን ገልፀዋል፡፡    

ኃላፊው ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፁት አለማየሁ መስከረም 21 ቀን ወደ ቡራ ወረዳ በመጓዝ ላይ ሳሉ ተይዘው ታስረዋል፡፡ በንጋታው ሀብታሙ እና ጌታሁን በዳይኔ ከተማ የፓርቲያቸውን ስራ በማከናወን ላይ እያሉ መታሰራቸውን ገልፀዋል፡፡ እስሩ የተፈፀመው ያል ፍርድ ቤት ማዘዣ በመሆኑ ድርጅቱ ድርጊቱን በፅኑ እንደሚያወግዝ አክለው አስታውቀዋል፡፡  

የሲዳማ ክልል መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ለማሰር በትኩረት እየሰራ ነው ያሉት አቶ ገነነ፣ ይህም የተወሰኑት እንዲደበቁ እያስገደዳቸው ነው ብለዋል፡፡ በማከልም “እነዚህ እስሮች ፓርቲው በክልሉ አስተዳደሮች የተስፋፋውን ሙስና እንዳይመረምርና እንዳያጋልጥ ለማደናቀፍ ያደረገው ሙከራ መሆኑን የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ያምናል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

“ፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙት ሶስቱ አባላቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ትክክለኛ ህጋዊ አሰራር እንዲኖር እንዲሁም አድሎዋ አያያዝ እንዲያበቃ ይሻል” ብለዋል፡፡ አባላቱ ለማስለቀቅ ጥረት ፓርቲው ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ መስከረም 21 ቀን በሲዳማ ክልል ወቅታዊ ክልላዊ ጉዳይን አስመልክቶ  ባወጣው መግለጫ የሲዳማ ህዝብ በክልል ከተደራጀበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በተደራጀ ሙስና፣ ብልሹ አሰራር፣ በፍትሕ እጦት፣ በህገወጥ እስራትና አፈና፣ የቡድን ሴራ ፖለቲካና ጎሰኝነትን መሠረት ባደረገ ቡድናዊ አስተዳደር ስረዓት በመጋለጡ የተነሳ ለተለያየ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ወድቋል ሲል ገልጧል።

የክልሉ አመራር በተከተለው በጎሰኝነትና ቡድናዊና አግይ አስተዳደር ስረዓት ምክንያት የህዝቡ አንድነት፣ አብሮነትና ማህበራዊ ዕሴት እየተሸረሸረ መጥቷል ሲል ገልፆ  ህዝቡ እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ፤ በከፋና ከሀገሪቱ ችግር አንፃር እንኳን ቢታይ እጅግ በጣም በባሰ ሁኔታ ለድህነት፣ ለረሀብ፣ ለጎዳና ተዳዳሪነትና ለልመና ተዳርጓል ብሏል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በመሆኑም ፓርቲው መንግስት ህግ በማስከበር ስም ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበርና የክልሉን ሰላም ለማናጋት የሚያደርገው እንቅስቃሴ በገለልተኛ አካል አጣርቶ ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button