ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ “በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች” በቁጥጥር ስር ውለዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12/2016 .ም፡ በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተካሄደ ጥምር ኦፕሬሽን ከአንድ ሺህ በላይ “በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች” በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

በአንድ ሳምንት የተካሄደው ልዩ ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በፌዴራልና በአዲስ አበባ ፖሊስ መሆኑን ኢቲቪ ዘግቧል።

ኦፕሬሽኑ በቡድን ተደራጅተው ወንጀል በሚፈፅሙ እና የሌባ ንብረቶችን በሚቀበሉ እንዲሁም በአደንዛዥ ዕፅ አስጠቃሚዎችና በቁማር ቤቶች ላይ መካሄዱ የጠቆመው ዘገባው በአዲስ አበባ ህብረተሰቡን ሲያማርሩ የቆዩ የወንጀል ተግባራትን ለመከላከል ያለመ መሆኑን አመላክቷል።

በኦፕሬሽኑ በርካታ ንብረቶችንም መያዝ መቻሉን ያስታወቀው ዘገባው የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች፣ ላፕቶፖች፣ የጦር መሳሪያዎች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ንብረቶች መሆናቸውን ጠቅሷል።

በሞተር ተሽከርካሪ፣ በሜትር ታክሲና በሿሿ የሚሰሩ ወንጀሎችን ለመግታትም ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል ያለው ዘገባው በአዲስ አበባ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የሕዝብ ስጋት እንዳይሆኑና ከተማዋን ፍፁም ሰላማዊ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።

ህብረተሰቡም ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማድረግ በሚሰሩ ስራዎች ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button