ዜና

ዜና፡ ቦርዱ ስድስተኛው ዙር ምርጫ ባልተካሄደባቸው አራት ክልሎች ምርጫ ለማካሄድ ከመንግስት በጀት አለመለቀቁን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ዙር ምርጫ ባልተካሄደባቸው አራት ክልሎች ምርጫ ለማካሄድ የሚውለው በጅት ከመንግስት አለመልቀቁን ገለጸ።

ቦርዱ ስድስተኛው ዙር ምርጫ ካደረገ ከሶስት አመታት በኋላ ምርጫ ሙሉ በሙሉ እና በከፊት ያለተደረገባቸው ቤንሻንጉል ጉምዝ፤ አፋር፤ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ቀሪና ድጋሜ ጠቅላላ መርጫ ለማደረግ መዘጋጀቱን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። 

ቦርዱ ምርጫውን ለማካሄድ ባዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የካቲት 22 ቀን ባካሄደው ውይይት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ሀይሉ፤ ቦርዱ የ6 ኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫውን ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለማካሄድ  አቅዶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸው ቦርዱ ለተግባራዊነቱ ከመንግስት የሚለቀቅለትን በጀት በመጠባበቅ ላይ ነው ብለዋል።

“በጀት መለቀቁ የግድ ነው” ያሉት ሰብሳቢዋ “ካለበለዚያ ከዚህ በላይ የሚያስኬድን አይደለም” ብለዋል። ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ቦርዱ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጸው ገንዘቡ በቅርቡ እንደሚለቀቅ ተስፋ አደርጋለው ሲሉ ተናግረዋል።

በአራቱም ክልሎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተም ቦርዱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መረጃ መወሰዱን እና ባብዛኛው አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ ምርጫውን ማካሄድ እንደሚቻል ሰብሳቢዋ ገለጸዋል። 

የ6ኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው የእጩዎች ምዝገባ ከሚያዚያ 7 እስከ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። የምረጡኝ ዘመቻ ከሚያዚያ 7 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሏል። የመራጮች ምዝገባ ደግሞ ከሚያዚያ 7 ቀን እስከ 27 2016 ዓ.ም ይደረጋል። የድምጽ መስጫ ቀን ደግሞ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ይሆናል ሲል ቦርዱ አስታውቋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button