ዜናቢዝነስ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ቻይና ለኢትዮጵያ የዕዳ ክፍያ እፎይታ እንደምትሰጥ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18/2015 ዓ.ም፡- በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከሚካሄደው የBRICS-Africa Outreach እና BRICS Plus ስብሰባ በፊት ጠ/ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ጽ/ቤታቸው አስታወቀ።

በውይይታቸውም ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በጋራ ማዕቀፍ ስምምነት መሰረት ቻይና ለኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023/2024 ጊዜ ውስጥ ለደረሰ የዕዳ ክፍያ እፎይታ እንደምትሰጥ መጠቆማቸውን የጠ/ሚኒስትር ቢሮ በማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመላክቷል።

በተጨማሪም መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ የበለጠ ትሥሥር ለመፍጠር ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል ብሏል።

ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ሀገራዊ ልማትን በመምራት ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር አድንቀዋል የለው ጽ/ቤታቸው በሰላምና በልማት ጥረቶች፣ በመልሶ ግንባታው ዘርፍ እንዲሁም ኢንቨስትመንቶችን እና የንግድ ግንኙነቶችን በማጎልበት ረገድ መሻሻልን እንደሚደግፉ ቃል መግባታቸውን አስታውቋል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ቻይና ላለፉት ዓመታት ለምታደርግላት ከፍተኛ ድጋፍ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች ብለዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት ለብዙ ዘርፎች ለጋራ ዕድገትና ልማት ጠንካራ መሰረት ነው ሲሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነትን ለማጠናከር ያለንን ቁርጠኝነት ለፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በድጋሚ ገልጬላቸዋለሁ ሲሉ በመልዕክታቸው አካተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button