ዜናUncategorizedቢዝነስ

ዜና፡ የፈረንሳይ የቢዝነስ ልዑካን በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11/2016 ዓ.ም፡- ሃያ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመለየት ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ፎሬንብሪፍ ድረገጽ በዘገባው አስታውቋል።

ባለፉት 24 አመታት የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የ84 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ማካሄዳቸውን የጠቆመው ዘገባው በዚህም ለአራት ሺ ሰዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን አመላክቷል።

በዛሬው ዕለት ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን የሚጀምሩት ኩባንያዎቹ ባሳለፍነው አመት ሰኔ ወር ላይ የፈረንሳይ የንግድ ቻምበር በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው አስታውቋል።

ባለፉት ግዜያት ኢትዮጵያ ተከታታይነት ያለው ፈጣን ኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧ እና የመስራት ፍላጎት ያለው ወጣት ሀይል ያላት መሆኑን የጠቀመው ዘገባው ሀገሪቱ በወደ አምባገነንነት የአመራር ዘይቤ እያጋደለች እንደምትገኝ እና የምዕራቡን አለም በመተው የምስራቁን አለም ካምፕ በመቀላቀል ላይ ትገኛለች ሲል ገልጿል።

በተያያዘ ዜና በጀርመን በርሊን ከተማ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የቡድን 20 ሀገራት መራሹ እና “G20 Compact with Africa (CwA)” በሚል ርዕስ በአፍሪካ ጉዳይ በሚመክረው ስብሰባ ለመታደም በርሊን የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ገጻቸው ባጋሩት መረጃ አስታውቀዋል።

ባጋሩት መረጃም ከኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ፕሬዝዳንት ማክሮንን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የተጠናከረው ግንኙነታችን ብሎም ዘርፈ ብዙው ትብብራችን በመተማመን እና ዘላቂነት ላለው ልማት ባለን የጋራ ፍላጎት መሰረት ላይ የፀና ነው ሲሉም  ገልጸዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button