ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በጎንደር በታጣቂዎችና በመንግስት ሀይሎች መካከል በተደረገ ውጊያ በርካታ ንጹሃን እና ታጣቂዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14/2016 ዓ.ም፡- ጎንደር ከተማ ትላንት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ሀይሎች መካከል በተደረገ ውጊያ በርካታ ንጹሃን እና ታጣቂዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። በከተማዋ በተካሄደው ውጊያ በሁለቱም ተፋላሚዎች ውገኖች በርካታ አባላት መሞታቸውንም ገልጸዋል።

የጎንደር ከተማ ኮማንድ ፖስት ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በከተማዋ “የጠላት ሀይል” ሲል የጠራቸው ታጣቂዎች ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታውቆ አመራሮችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሙትና ቁስለኛ አድርጊያለሁ ብሏል። የመንግስት ሀይሎችን እርምጃ መቋቋም ያቃተው ታጣቂዎቹ ከተማዋን ለቀው ሸሽተዋል ሲል ገልጿል።

መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ በፋኖ ስም የሚነገደው “ፅንፈኛ ሃይል” ሲል የጠራው ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ ክሩቤል ክንዱ መልካሙ፣ መልካሙ አበባው (የተሾመ አበባው ወንድም)፣ እሸቴ (የሀብቴ ምክትል) እና ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ 2 አመራሮችን መግደሉን አስታውቋል። መከላለያ ሰራዊት የሞቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም አክሎ ገልጿል።

ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪ በከተማዋ በቅርቡ የተሾሙ ሶስት የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች፣ የሚሊሻ ሃላፊዎች ከነአጃቢዎቻቸው መገደላቸውን ገልፀው በአሁኑ ግጭት ከሁለቱም ወገን በርካታ ታጣቂዎች መሞታቸውንም ተናግረዋል።

በትላንትናው ዕለት በነበረው ውጊያ ከተገደሉት የፋኖ አመራሮች መካከል አንዱ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ህክምና መከልከሉን ከቅብ ጓደኞቹ መረዳታቸውን የገለጹት የከተማዋ ነዋሪ የጎንደር ሆስፒታል ለነዋሪዎች ዝግ መደረጉን እና ምንም አይነት አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ከግጭቱ በኋላ ከትላንት ማታ ከሁለት ሰዓት በኋላ የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን አክለው ገልፀው በከተማዋ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር የጥይት ድምጽ አይሰማም ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሁኔታውን አስመልክቶ አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡ እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጎንደር ዩኒቨርስት መምህር በበኩላቸው ከተማዋ ውስጥ ትላንት ከፍተኛ ውጊያ እንደነበር ገልጸው ክልሉ ወደ አስጊ ሁኔታ እያመራ ነው ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተዋል።

ክልሉ ሰላም ከራቀው ወራቶች መቆጠራቸውን የጠቀሱት መምህሩ በጎንደርም ሆነ በተቀረው የክልሉ አከባቢዎች ለወራት የነበረው ሁኔታ የታፈነ ሰላም (Suppressed peace) ነው ብለዋል፡፡ “በድሮንና በታንክ በማስፈራራት በሚሊተሪ ብዛት የታገዘ እና የተያዘ ሰላም ነው ያለው” ብለዋል። አንጻራዊ የምትለው ሰላም እራሱ አልነበረም፣ በፕሮፓጋንዳ እና በሴራ የታገዘ ሰላም ነው የነበረው ሲሉ ገልጸዋል።

መከላከያ ሰራዊት በመግለጫው ታጣቂ ቡድኑ በከተማዋ ቀበሌ 18 አካባቢ ክፍለ ከተማውን ማቃጠሉን እና የሸማቾች የህብረት ሥራ ማህበር ስኳር ዘይትና መሠል ፍጆታዎችን የመዝረፍ ተግባር ፈፅሟል ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button