ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የፌደራል መንግስቱ ተቋማት በምዕራብ ትግራይ የህዝብ አሰፋፈር ለመቀየር ተሳትፎ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሪፈረንደም አይታሰብም – ጌታቸው ረዳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5/2016 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት የካቲት 5 ቀን 2016 ቀን ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምዕራብ ትግራይ የፌደራል መንግስቱ ተቋማት የአከባቢውን የህዝብ አሰፋፈር እንዲቀየር እየሰሩ ባለበት እንዲሁም በአከባቢው ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሁንም በተጨማሪ እየተፈናቀሉ ባለበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማካሄድ የማይታሰብ ነው ሲሉ ጠቁመዋል። ሪፈረንደም የሚካሄድ ከሆነም በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ህገመንግስቱን ተከትሎ ነው ብለዋል።

ተፈናቃዮች ሰላማቸው እና ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ መጀመሪያ ወደቀያቸው መመለስ ይቀድማል፣ እራሳቸውን ማስተዳደር የሚችሉበት ሁኔታ እንፍጠር፣ ሁለቱም ህዝቦች ወደ ግጭት እንዳይገቡ የሚያደርግ ሁኔታዎችን እንፍጠር የሚል ሀሳቦችን አቅርበናል ሲሉ ገልጸዋል።

በተለይም በምዕራብ ትግራይ በተደራጀ ሁኔታ በርካታ አዳዲስ ሰፋሪዎች እንዲሰፍሩ እየተደረገ ባለበት፣ ይህንን የህዝብ አሰፋፈር የፌደራል መንግስት ተቋማት ጭምር የተሳተፉበት በሚታይ ሁኔታ እያሳለጡ በሚገኝበት፤ ከአከባቢው ተፈናቅለው ያሉ ሰዎችን መመለስ ቀርቶ አሁንም በመካሄድ ላይ ያለው ነዋሪዎችን የማፈናቀል ተግባር በቀጠለበት እንዲሁም በአከባቢው የተፈጸመው ውድመት ከፍተኛ ተግዳሮት በሆነበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማካሄድ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ብለዋል። የተሻለ ሁኔታ እንኳን ቢኖር ጭምር በስራ ላይ ያለው የጊዜያዊ አስተዳደር በመሆኑ ሪፈረንደም ማካሄድ አይቻልም ሲሉ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ስለነበራቸው ውይይት በገለጹበት ወቅት ዋነኛ አጀንዳችን የፕሪቶርያው ስምምነት አተገባበር ነበር ብለዋል። ከምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እስካሁን ላለመመለሳቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስቱን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን የፌደራል መንግስቱ በበኩሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መስራት የሚጠበቅበትን አልሰራም ሲል ወቀሳ ማቅረቡንም አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል።

የሰላም ስምምነቱን እን ግዜ መግዣ በመጠቀም ሌላ አጀንዳችሁን ለማስፈጸሚያነት እያዋለችሁት ነው፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከኤርትራ እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልል ታጣቂዎች ጋር በጋራ በመሆን የፌደራል መንግስቱ ላይ እያሴራችሁ ነው የሚል ወቀሳ ከመንግስት በኩል እንደቀረበባቸው ጠቁመዋል። ለዚህም በጊዜያዊ አስተዳደሩ በኩል የተሰጠው ምላሽ የትግራይ ህዝብ ዋነኛ አጀንዳ ሰላማችንን መመለስ ነው፣ ተፈናቃዮቻችንን ወደ ቀያቸው ከመመለስ የበለጠ አጀንዳ የለንም የሚል መሆኑን ገልጸዋል።

ህወሓት የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል መሆኑን አስታውቀው የፌደራል መንግስቱ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አማካኝነት ህወሓትን ከፓርቲነት መሰረዙ የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንቅስቃሴ ላይ ችግር መፍጠሩን አመላክተዋል።

የህወሓትን ተመልሶ በምርጫ ቦርድ እውቅና ስለማግኘት የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ በምላሻቸው የፌደራል መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንደማይደግፈው፣ ህወሓት እያሉ መግለጫ እያወጡ ህወሓት የሚባል አናውቅም የሚል ንግግር ሊኖር አይችል መባሉን አስታውቀዋል። ያሉትን የህግ እንቅፋቶች ቶሎ በማሰቀረት ህወሓት ህጋዊ ህልውናው የሚረጋገጥበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት ተረዳድተናል፤ የፍትህ ሚኒስቴር ጉዳዩን እንዲከታተለው እና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ሃላፊነቱ ተሰጥቶታል ብለዋል። በአጭር ግዜውስ ይደረጋል ሲሉ አስታውቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በቀጣይ ሳምንታት የአፍሪካ ህብረት፣ የመንግስታቱ ድርጅት፣ የአሜሪካን እና የደቡብ አፍሪካ መንግስታት ተወካዮች ተሳታፊ የሚሆኑበት የፕሪቶርያውን ውል አፈጻጸም የተመለከተ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button