ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መነኮሳት ላይ የተፈጸመውን ግድያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አወገዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18/2016 ዓ.ም፡- በኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መነኮሳት አባቶች ላይ የተፈፀመውን ግድያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አወገዘ።

ጉባኤው ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “በሃይማኖት ተቋማትና አባቶች ላይ የሚደርሰውን በደል፣ ግፍና ግድያ በጽኑ እያወገዝን መንግስት ለተቋማቱ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደረግ በአጽንኦት እንጠይቃለን፤” ብሏል።

ስለደረሰው ጥቃትም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ አገልጋዮችና ምዕመናን እንዲሁም ለገዳማውያኑ በሙሉ መጽናናትን ተመኝቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሃይማኖት ተቋማትና አባቶች ላይ ጥቃትና የግፍ ግድያ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ያስታወቀው ጉባኤው በተቋማቱ ላይ የሚፈፀመው ጥቃት፣ የግፍ ግድያ፣ ኢሰብኣዊ አያያዝ እና መዋቅራዊ በደል ሁሉ የተወገዘ ተግባር ከመሆኑም በላይ ሕጋዊ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ኢፍትሀዊ ተግባር ነው ብሏል።

ጉባኤው በመግለጫው የበላይ ጠባቂ አባቶች ያስተላለፉትን ባለአምስት ነጥብ አቋም አስቀምጧል።

ግድያው ተጣርቶ አጥፊ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቀው ጉባኤው በቀጣይም በስጋት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎች የሃይማኖት ተቋማትም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው አሳስቧል።

የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት የሃይማኖት ተቋማትንና መዋቅራቸውን ለፖለቲካዊና ለርዕዮተ-ዓለማዊ ተልዕኮው መጠቀሚያ ባለማድረግ የሃይማኖት ተቋማት መንፈሳዊ ነፃነታቸው እንዲከበርና እንዲያስከብር አበክረን እንጠይቃለን ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በየትኛውም ደረጃ በሚገኙ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ የሃይማኖት መሪዎች፣ አባቶችና አስተማሪዎች ከመሠረታዊ የሃይማኖታቸው አስተምህሮ በሚቃረን መልኩ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሁነው የትኛውንም ፖለቲካዊ አቋም ከማራመድ እንዲቆጠቡ በአጽንኦት አሳስቧል።

በመጨረሻም መንግስት የዜጎችን የመንቀሳቀስ ሕገ መንግስታዊ መብት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤው በመግለጫው ጠይቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button