ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት የምግብ እርዳታና የማዳበሪያ ስርጭት በመስተጓጎል ላይ ይገኛል 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል እየተሄደ ባለው ግጭት መንገዶች በተደጋጋሚ መዘጋታቸው ምክንያት በዋግኅምራ ዞን በተከሰተው ድርቅ ለከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ለተጋለጡ ወገኖች የተላከው የምግብ እርዳታ ከሁለት ሳምንታት በላይ በማዘግየት ከፍተኛ መስተጓጎል አስከትሏል። 

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የስራ ኃላፊ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ላጋጠመው ድርቅ የምግብ ዘይትና አስቸኳይ የምግብ አቅርቦቶችን የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ሰፍራው ቢልክም ባህርዳረ ላይ ባጋጠመ የፀጥታ ችግር ምክንያት የተላከው እርዳታ ከሁለት ሳምንት በላይ መንገድ ላይ ቆይቷል ብለዋል፡፡ 

የማህበሩ የሰብአዊ ዲፕሎማሲ እና የግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መስፍን ደረጀ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት ግጭቱ ወሳኝ የዕርዳታ አቅርቦቶችን በቀጥታ የሚያደናቅፍ ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት በነበሩት ግጭቶች መንገዶች በመዘጋታቸው በክልሉ በተለያዩ ከተሞች ዕርዳታ እንዳይደርስ ማደረጉን ጠቅሰዋል።

አቶ መስፍን በዋግ ኽምራ በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች የሚውል ተጨማሪ እርዳታ ለማድረስ ቢታቀድም በክልሉ ባለው የጸጥታ ሁኔታ የተነሳ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም ብለዋል፡፡

ባአንጻሩ አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በዋግ ኽምራ ዞን አበርገሌና ፅግበጂ ወረዳ ለሚኖሩ ለ25,140 ከስደት ተመላሾች እና የአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን በዛሬው ዕለት አስታውቋል። ኮሚቴው አስፈላጊ አገልግሎቶች በሌሉበት ወይም ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ሌሎች አካባቢዎች ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን እየረዳ መሆኑን ገልጿል።

በዋግ ህምራ ዞን ባጋጠመ የዝናብ እጥረት ሰሃላ ወረዳን ጨምሮ የውሃ እጥረት፣ የሰብል ምርት ላይ ጉዳት መድርስ እና የእንስሳት ሞት ጋር ሲታገል ቆይቷል።

በሰሃላ ወረዳ የተማሪዎች ቁጥር የቀነሰ ሲሆን፣ የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ውሃ ፍለጋ እና የስራ እድል ፍለጋ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ 1,688 ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ለአፈር ማዳበሪያ ስርጭት መሰናክል ኾኗል ነው የተባለው። የክልሉ ግብርና ቢሮ ከጁቡቲ ወደብ ማጓጓዝ የተጀመረውን የአፈር ማዳበሪያ ለክልሉ ለማቅረብና ለማሰራጨት ችግር እየገጠመው መኾኑንም አስታውቋል፡፡

ቢሮው የአፈር ማዳበሪያው በዝርፊያ ላይ በተሰማሩ “ፀረ ሰላም ሀይሎች” ምክንያት መንገድ ላይ እየተዘረፈና እየተመዘበረ ነው ሲል ገልጾ ይህም የተገዛውን የአፈር ማዳበሪያ በጊዜውና በወቅቱ ለመስኖ እርሻ ልማት እንዲውል ተደራሽ ማድረግ እንዳይቻል እያደረገ ነው ብሏል፡፡ አክሎም ማህበረሰቡ ከመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ጎን በመሆንና በመተባበር ለክልሉ ድርሻ  የተገዛውን የአፈር ማዳበሪያ ለመስኖ እርሻ ልማት እንዲደርስ አንዲተባበር ጠይቋል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት መደበኛ የትምህርት እንቅስቃሴ በወቅቱ እንደማይጀምሩ አድርጓል። በተያዘው የትምህርት አመት በጸጥታ ችግር ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ተማሪዎች 50 በመቶ የሚጠጉት መሆናቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ መናገራቸውን አሚኮ በዘገባው አመላክቷል። 

በክልሉ ምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አሁንም ድረስ ትምህር አለመጀመሩን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አስታውቀዋል።

በእነዚህ ዞኖች ውጭ በሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች 60 በመቶ የአንደኛ ደረጃ እና 55 በመቶ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ብቻ በመማር ላይ እንደሚገኙ ያመላከተው ዘገባው ለዚህ ደግሞ የጸጥታው ችግር አሁንም ሥጋት መኾኑን በምክንያትነት ሃላፊዋ ማስቀመጣቸውን አካቷል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button