ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ከ300 በላይ የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች መንግስት በአማራ ክልል ላይ የጣለውን የኢንተርኔት እገዳ እንዲያነሳ፤ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3 / 2016 ዓ.ም፡- ከ300 በላይ የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል ላይ የጣለውን የኢንተርኔት ( በይነ-መረብ) እገዳ እንዲያነሳ ጠይቀዋል፡፡ ከ105 ሀገራት የተወጣጡት  ኪፕኢትኦን  ጥምረት ድርጅቶቹ በግጭት ወቅት ኢንተርኔት መዝጋት የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል እና አስፈላጊ መረጃን እንዳያገኙ ያደርጋል ብለዋል፡፡ በክልሉ ከነሃሴ ውር ጀምሮ የተወሰደው ኢንተርኔት መዝጋት ተግባር የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ድርጊት ነው ሲሉ ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በመግለጫቸው “ግጭት እየተባባሰ እና የፀጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በሄደ ቁጥር በክልሉ ያሉ ሰዎች ከተቀረው አለም ጋር በመገናኘት የተፈፀመ ሞት እና የመብት ጥሰቶችን ማሳውቅ ያስፈልጋል” ነው ያሉት፡፡

መብግስት ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የሚገልፅ ሪፖርቶች እንደደረሱት አስታውቋለ፡፡ ኢሰመኮ በክለሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በተከሰተው ግጭት ሞት እና በንፁሃን ላይ ጉዳት አድርሷል ብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጽ/ቤት ከሀምሌ ወር ጀምሮ 183 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል ሲል ገልጧል፡፡ እንደ ባንክ፣ ስልክ፣ የህክምና፣ ትምህርት ያሉ አገልግሎቶች መስተጓጎላቸውን እና መንገዶች መዘጋታቸው የሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈናቃዮች እንዳይደርስ መድረጉን ድርጅቱ አክሎ ገልጧል፡፡

ግጭት እና ቀውስ ሲያጋጥም የኢትዮጵያ መንግስት ኢንተርኔት ሲዘጋ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ያለው የድርጅቶቹ የጋራ መግለጫ በትግራይ ክልል ተከስቶ በነገረው ግጭት ኢንተርኔት ተዘግቶ መቆየቱን አስታውሷል፡፡ ኪፕኢትኦን አ.አ.አ ከ2016 ጀምሮ ከግጭት፣ ፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ 26 ጊዜ መዘጋቱን ገልፆ በ2023 ብቻ የኢትዮጵያ መንግስት ሶስት ጊዜ እንተርኔት ዘግቷል ሲል ከሷል፡፡

ድርጅቶቹ፣ የሲቭል መህበረሰብ ድርጅቶች በአማራ ክልል ተዘግቶ የቆየውን ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያወግዙ እና ግጭትን እና አለመረጋጋትን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button