ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአማራና ትግራይ መካከል “አከራካሪ በሆኑ” አከባቢዎች ሳቢያ ግጭት እንዳይንሳ ከህዝበ ውሳኔ ውጭ ሌላ የመፍትሄ ሀሳበ ካለ መንግስት በደስታ ይቀበላል- ጠ/ሚ አብይ አህመድ  (ዶ/ር) 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4/ 2016 ዓ ም፦ በአማራ እና ትግራይ መካከል “አከራካሪ በሆኑ” አከባቢዎች ሳቢያ ግጭት እንዳይንሳና ዘላቂ ስላም እንዲስፍን ከህዝበ ውሳኔ ውጭ ሌላ የመፍትሄ ሀሳበ ካለ የፌዴራል መንግስት በደስታ የሚቀበል መሆኑን ጠ/ሚ አብይ አህመድ  (ዶ/ር) ገልጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይህን ያሉት አየተካሔድ ባለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ለተኑሱላቸው ጥያቄዎቸ ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለቱ ክልሎች መካከል “አከራካሪ የሆኑ” ጉዳዮችን በህዝበ ውሳኔ ለመፍታት የፌዴራሉ መንግስት የሁለቱ ክልል አመራሮችንና ህዝቡን ማወያየቱን ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሁለቱ ክልሎች አከራካሪ በሆኑ አካባቢዎች የሚነሳውን ክርክር ለመፍታትና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መንግስት ህዝብ ውሳኔን እንድ መፍተሄ ማቅርቡን ገልጸው ነገር ግን የአማራና የትግራይ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች ተወያይተው ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ መፍትሄ አለን ካሉ መንግስት በደስታ የሚቀበል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቀላይ ሚኒስተሩ በማብራሪያቸው “መፍትሄ ሳናመጣ የመጣውን የምፍትሄ ሀሳብ የማንቀበል ከሆነ ግን ወደ ሰላም አይወስድም” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራና በኦሮሞን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ሁለቱ ህዝቦች ፈለጉም አልፈለጉም በሰላም ለመኖር ያላቸው ምርጫ አንድ ብቻ ነው ሲሉ ገልጸው ይህም የአንድ አባት ልጆች ፣ የአንድ ሀገር ዜጎች ወንድማማቾች መሆናቸውን አውቀው በሰላም በተከባበረ አብሮ መኖር በሚያስችል ማንነት መጉዋዝ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በዶላር ከመገዳደል በሀሳብ መገዳደር ይሻላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ውጭ ምንዛሬ እጥረት አለ እንላለን  በዶላር የተገዛ ጥይት ስንተኩስ እንውላለን፣ ይህ ሰው የሚገድል ብቻ ሳይሆን ወደ ፊትም ቀና እንዳንል የሚያደርገን ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ከሁሉ በላይ በዚህ አላማ ውስጥ የተሰበሰቡ ሰዎች ምንም የሚያሳኩት ነገር እንደሌለ ጠቅሰው ወደ ሰላም፣ ወደ ውይይት መሄዱ ትልቅ አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button