ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ የመልከአ ምድር እስረኛ መሆን ይበቃታል ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አብይ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3/2016 ዓ.ም፡- ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል፣ በቀይባህር ዙሪያ ልትመክር ይገባታል ሲሉ ገለጹ። ጠ/ሚኒስትሩ ከሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ባካሄዱት ውይይት እና በሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በተላለፈው 45 ደቂቃ በወሰደው ገለጻቸው እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ በ2030 150 ሚሊየን ህዝብ እንደሚኖራት ጠቁመው ይሄ ህዝብ የመልከአ ምድራዊ አቀማመጥ እስረኛ ሊሆን አይገባም፣ አይቻልም ብለዋል ምክንያቱ ደግሞ ድህነት አለ የሆነ ግዜ ላይ ብንፈልግም ባንፈልግም መፈንዳቱ አይቀርም ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ህዝቡ እንዳይበተን የባህር በር ማግኘት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ መነጋገር እና መልክ ማበጀት ያስፈልጋል ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ በገለጻቸው ሰፈሩ በሙሉ ሲሉ የገለጹት ቀጠናውን ሰላም እንዲሆን መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ሲሉ በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን ቅድሚያ ሰጥተው የገለጹት ቀይባህርን ነው። የቀይባህር ጉዳይ በደንብ ንግግር ያስፈልገዋል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ አናነሳውም አንናገርም ማለት አንችልም፣ እንደዚህ አይነት አቋም አንፈልግም እናነሳዋለን ብለዋል።

የባህር በር ባለቤትነት ሁለንተናዊ እይታ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ገለጻ ግብጽ እና ሱዳን አባይ ህልውናችን ነው ካሉ ኢትዮጵያም ቀይባህር ህልውናየ ነው የማለት መብት አላት ሲሉ ገልጸዋል። ቀይባህር እና አባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ፣ ለኢትዮጵያ እድገት እና ጥፋት መሰረት ሲሉ ተደምጠዋል።

በጥቅሙ ዙሪያ ልክ ህዳሴ ግድብ ላይ እንደምነደራደረው መደራደር እንችላለን ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ድርድር ማለት አትጠቀምበት ማለት እስካልሆነ ድረስ ችግር የለውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ በታሪክ፣ መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ በኢኮኖሚ እና በዘር ህጋዊ የሆነ ጥያቄ አላት የሚል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር የሰፈረ ስምምነት ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። ይህንን ስምምነት መፈተሽ ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀይ ባህር ጉዳይ የማንወያይ ከሆነ በስንዴም በአረንጓዴ ልማትም መነጋገር ማቆም አለብን ብለዋል። በአባይ ጉዳይ ማንም ፈርቶን አያውቅም ከኛ ጋር መነጋገር ይፈልጋል ሲሉ በንጽጽር አቅርበዋል።

ወደ ቀይ ባህር ስንቀርበ ታላቅ ነበርን ሲሉ ታሪካዊ ዳራ ነው በማለት በማጣቀሻነት ሲያቀርቡ የተደመጡት ጠ/ሚኒስትሩ በግዜ ሂደት መራቃችን ይሄንን እንዳሳጣን አመላክተዋል። ዋናው ችግር የሚመጣው እንዴት ነው ወደ ቀይባህር የምንቀርበው የሚለው ጥያቄ ነው ሲሉ ተናግረው፣ 120 ሚሊየን ስለሆንኩ ጉልበት ስላለኝ፣ መከላከያ ስላለኝ፣ አየር ሀይል ስላለኝ ነው ወይ የምቀርበው ሲሉ በመጠየቅ በዚህ መልኩ መሆን የለበትም፣ ማድረግ የለብንም ሲሉ ገልጸዋል፤ በጦርነት እንዳይሆን ተብሎ ደግሞ እውነታውን መደበቅ ትክክል አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል።  

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በህዝብ አሰፋፈርን በገለጻቸው ወቅት በማቅረብ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚገባት የሞገቱት ጠ/ሚኒስትሩ የአፋርን እና የሶማሌ ህዝብን አሰፋፈር በማሳያነት አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ወደብ ለማግኘት ለጎረቤቶቿ ከህዳሴ ግድብም ይሁን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ መስጠት እንደምትችል በገለጻቸው አመላክተዋል።

ይህንን ለማሳካት ምንድን ነው ያለን አማራጫ በሚል በውይይታቸው ማጠናቀቂያ ባቀረቡት ሀሳብ ላይ በመጀመሪያ የገለጹት ስለ ፌደሬሽን እና ኮንፌደሬሽን ሲሆን በቀድሞ ግዜ ኢትዮጵያን እና ኤርትራን ያጣላው የኮንፌደሬሽን ህግ አሁን ሊታይ ይችላል ብለዋል። ሌላኛው ያቀረቡት አማራጭ ደግሞ የመሬት ልውውጥ ነው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button