ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ለምርት ዘመኑ ከውጭ ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለፀ  

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2/2016 ዓ.ም፡- ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጭ ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ የኢትዮጵያ የባህር፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ለምርት ዘመኑ ከውጭ ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 610 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ተጨማሪ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጂቡቲ ወደብ መድረሷን የጠቆመው ድርጅቱ የማዳበሪያውን መምጣት ተከትሎ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሰባት ዙሮች ከውጭ የተጓጓዘው የማዳበሪያ መጠን ወደ 3 ሚሊዮን 310 ሺህ ኩንታል ከፍ ማለቱን አስታውቋል።

ከዚህ መጠን ውስጥ እስከአሁን 2 ሚሊዮን 40 ሺህ 479 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደር ዩኒየኖች በመሰራጨት ላይ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም 520 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ እንዲሁም ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም 390 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን እና 160 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ማዳበሪያ የጫኑ ሁለት መርከቦች ወደብ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁሟል።

ባለፉት ተከታታይ አመታት መንግሥት ተፈላጊውን የአፈር ማዳበሪያ አላቀረበብ በሚል መተቸቱ ይታወሳል። በመንግስት በኩል የሚፈለገው የማዳበሪያ መጠን ባለመቅረቡ ከነጋዴዎች በእጥፍ ዋጋ ለመግዛት መገደዳቸውን አርሶ አደሮች በወቅቱ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ማዳበሪያ በአግባቡ አልደረሰንም ያሉ አርሶ አደሮች በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ጅራፍ በማጮህ ማዳበሪያ እንዲቀርብላቸው በሰላማዊ ሠልፍ መጠየቃቸው ይታወሳል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button