ዜናህግ እና ፍትህ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የዘጠኝ ዓመት ልጅ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ፖሊስ እየመረመረ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25/ 2015 ዓ.ም፡- በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ነሃሴ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ፋጡማ ኢጋስ የተባለች የዘጠኝ ዓመት ልጅ ላይ በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተፈፀመባትን አስገድዶ የመድፈር እና አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ፖሊስ እየመረመረ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ድርጊቱ ከተፈፀመባት በኋላ የታጡማ አስክሬን ለምርመራ ወደ ጅግጅጋ ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዱን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አብዲቃዲር ራሺፍ ገልፀጸዋል፡፡ ሃላፊው አክለውም የሆስፒታሉ ዶክተሮች በሰውነቷ ላይ የፆታዊ ጥቃት ምልክቶች በማግኘታቸው ወደ ካራማራ ሆስፒታል ልከዋታል ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ ከመገደሏ በፊት መደፈሯ በህክምና ምርመራው ተረጋግጧል ነው ያሉት።

“በአሁኑ ወቅት ከግድያው ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። የመጀመርያው መረጃ እንደሚያመላክተው ከአራቱ ሰዎች መካከል አንዱ በሰውነቱ ላይ በሚስማር ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ በድርጊቱ ላይ ተሳትፎ ሊኖረው ይችላል በሚል ተጠርጥሯል። ምርመራው እየተከናወነ በመሆኑ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ እናሳውቃለን፡፡” ብለዋል አቶ አብዲቃድር።

የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አብዲቃዲር “ድርጊቱን የፈፀሙት ሶማሊ ያልሆኑ ግለሰቦች ናቸው በማለት ፖለቲካ ፓርቲዎች  በሀሰት በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክት እሰራጭተዋል፤ ሁከትና ግጭት ለማስነሳት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም” ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አክለውም ከተማዋ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ መሆኗንና ነዋሪዎቿም የለትተለት እንቅስቃሴያቸውን እያከናወኑ መሆንን የተናገሩት ኃላፊው “አንዳንድ ሰዎች ለራሳቸው ደህንነት ሲባል በቁጥጥር ስር የነበሩ ቢሆንም በኋላ ላይ ግን ተለቀዋል” ሲሉም ገልጧል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የፋጡማን ቤተሰቦች ለማነጋገር ያደረግነው ሚከራ ባለመሳካቱ የእነሱን ሀሳብ ማካተት አለተቻለንም፡፡ አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button