ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት “የፖሊስ ሰራዊቱን ለመከፋፈል” የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ፖሊስ እንደማይታገስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8/ 2016 ዓ/ም፡_ ወቅት እና አጋጣሚዎችን እየጠበቁ ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” ህዝቡን ለማሸበር  እና የፖሊስ ሰራዊቱን ለመከፋፈል” የሚደረጉ ሃላፊነት የጎደላቸውን እንቅስቃሴዎች ፖሊስ እንደማይታገስ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ትላንት አምሻሹን ባወጣው መግለጫ፣ “የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ ብሔር ተወላጆች የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ብቻ ያተኮረ  እርምጃዎችን ሊወስድ እንዳሰበ የሚገልፅ ይዘት ያለው ሃሰተኛ ደብዳቤ ልዩ ልዩ ህገ-ወጥ ቴክኒኮችን በመጠቀም በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲያዘዋወሩ ተስተውሏል” ብሏል።

መረጃው “ፀረ ሰላም” ሃይሎች ሲል የጠራቸው አካላት ወቅትና አጋጣሚዎችን በመጠቀም የራሳቸውን አጀንዳ ለማሳካት ያሰራጩት ሃሰተኛ መረጃ ነው ሲል ፖሊስ አጣጥሎታል። 

እውነታውን መላው የተቋማችን አመራርና አባላትም ሆነ በከተማዋ ነዋሪዎች የሚታወቅ ነው ሲለ ገልጾ ለተሰራጨው ሃሰተኛ መረጃ ቦታ ባለመስጠት ሁከት እና ግጭት ለመፍጠር እንዲህ አይነቱን ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በማጋለጥ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ተቀናጅተው ይሰራሉ ብሏል።፡፡ 

አዲስ አበባን “የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል” ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ግጭት ጠማቂ ሃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ያደረጓቸው መሰል ሙከራዎች በፀጥታ ሃይሉ እና በሰላም ወዳዱ ነዋሪ መክሽፉን ፖሊስ በመግለጫው አክሎ አስታወቋል። 

ነዋሪው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሰላምን ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚከናወኑ ተግባራትን በማገዝ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button