ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ለማክሸፍ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ 

አዲስ አበባ፣ ጥር 7/ 2016 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ለማክሸፍ የአሜሪካ መንግስት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር “ታሪካዊ ትብብር” እያደረግ መሆኑን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በተካሄዱ ጦርነቶች ጋር ተያይዞ የተቀበሩ ፈንጂዎችን እና ከባድ የጦር መሳሪያሪዎች የንጹሃን ዜጎች ህይወት መጥፋትን እያስከተለ መሆኑን እና አርሶ አደሮች ወደ እርሻ ስራቸው እንዳይመለሱ መደረጉን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ ገልጿል። 

በተጨማሪም የጦር መሳሪያ ቅሪቶቹ ለዕለት ተለት ክንውን ስጋት መፍጠራቸውና የቀደሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና መልሶ ማቋቋም (DDR) ሂደት ላይ እንቀፋት መፍጠሩ ተገልጿል።

ይህንንም ለመቅረፍ ቢኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ የጸጥታ ትብብር ጽ/ቤት እና አሜሪካ መከላከያ ዲፓርትመንት ከኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት እና ከኢትዮጵያ ፍንጅ አምካኝ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ጥር 6 እና 7 ተትኳሾችን ለማክሽፍ የመስክ ዳሰሳ ጥናት ማደረጋቸው ተገልጿል። 

የዳሰሳ ጥናቱ የሲቪሎችን ደህንነትን እና የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል በመላው ኢትዮጵያ በጦርነት ወቅት የቀሩ ተተኳሾችን መጠንን ለመለየት ይረዳል።

የዚህ ትብብር ዋና ዓላማ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለኢትዮጵያ ፍንጅ የማምከን ጽ/ቤት ማቅረብ መሆኑን የገለጸው መግለጫው በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ መሳሪያዎችን የማቅረብ፣ ስልጠናዎችን የመሰጠት እና ተጨማሪ ሀብቶችን የማቀረብ ስራ ይጀምራል ብሏል።

በኢትዮጵያ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩና ጉዳት እያደረሱ ያሉ ፈንጂዎችን የማጽዳት እና የማስወገድ ተግባር ሊፋጠን እንደሚገባ እና መንግሥት ለፈንጂ ተጎጂዎች የማቋቋም እና የተሐድሶ አገልግሎት ድጋፎችን ማቅረብ እንዳለበት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ማሳሰቡ ይታወሳል

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ከተከሰተው ጦርነት ተከትሎ ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች፣ በእርሻ፣ በውሃ መቅጃ እና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም የትምህርት ወይም የጤና ተቋማትን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ሕይወት ወደሚከወኑባቸው ሥፍራዎች በሚወስዱ መንገዶች አካባቢ የተቀበሩ ፈንጂዎች፣ የተጣሉ ቦምቦች፣ የከባድ መሣሪያ ቅሪቶች እና በቀላል ንክኪ የሚፈነዱ ሌሎች መሣሪያዎች በሰዎች ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛል ብሏል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button